የእግዚአብሔር ፍቅር ተፈጥሮ

የእግዚአብሔር ፍቅር ተፈጥሮ

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለ ሆነ ፣ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርሰቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን ፣ በጸጋ ድናችኋልና ፣ – ኤፌሲዮን 2:4-5

አንዳዴ ሕይወት በሚያበሳጭ ሁኔታ ውስጥ ስታልፍ ለራሳችን ማድረግ የምንችለው ምርጡ ነገር የእግዚአብሔር ፍቅር ተፈጥሮን ማስታወስ ነው፡፡

በጣም ማራኪ ከሆኑ የመጽሀፍ ቅዱሳችን ክፍሎች ውስጥ አንደኛው ገና ሀጢኣተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ (ሮሜ 5፡8 ተመልከት) የሚለው ክፍል ነው፡፡ ፍቅሩ እስከሚገባን ድረስ አልጠበቀንም፡፡ ያልምንም ቅደመ ሁኔታ ወደደን፡፡ እውነቱን ለመናገር ብዞቻችን ይህንን ለመረዳት እንቸገራለን ምክንያቱም እኛ በሕይወታችን ምንም ነገር በነጻ ማግኘት አልተለማመድንም፡፡

ከታላቅ ፣ አስደናቂ እና ጥልቅ ከሆነ ለእኛ ፍቅር የተነሳ እግዚአብሔር ሕይወቱን እኛ በነጻነት አፈሰሰው፡፡ ይህ ልዩ ፍቅር ነው ፤ እውነተኛ ልዩ ፍቅር ራስን አሳልፎ ከመስጠት የሚበልጥ የሚያረካው ስላላገኘ ነው ራሱን የሰጠው፡፡

ቅደመ ሁኔታ የሌለበት የእግዚአብሔር ፍቅር ነው ወደ እሱ የሳበን ፤ አስደናቂ ጸጋው ሀጢኣታችንን ሁሉ ደመሰሰ እናም የእርሱ ሃይለኛ መስዋት ነው ለእኛ ወደሱ እንድነቀርብ መንገድ የከፈተልን፡፡ ፍቅሩ መቼም አይቋረጥም ፣ በፍጹም ተስፋ አይቆርጥም መቼም አይተዋችሁም ፡፡ ዝቅታ ወይም ድብታ ሲሰማችሁ ይህን አስታውሱ እግዚአብሔር ስለ እናን ታላቅ ፍቅር አለው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ባይመስለኝም እንኳን ለኔ ያለህ ፍቅር ፈጽሞ አይቋረጥም፡፡ ሁሉ ነገረህን ሰጥተኸኛል፡፡ ያላንዳች ጥርጥር እንደምትወደኝ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon