
እግዚአብሔር የሀይልና የፍቅር፣ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና፡፡ – 2 ኛ.ጢሞ 1፡7
በእያንዳንዱ ቀን ሰይጣን ሊጭንብን የሚሞክርብን አድካሚ ፍርሀት አለ፡፡እኔ ፍርሀትን “የውሸት ማስረጃ የእውነት መስሎ ሲቀርብ” ብዬ ነው የምጠራው፡፡እግዚአብሔር እንዲኖረን ከሚፈልገው ሀይል፣ፍቅር እና የሚያገናዝብ አዕምሮ እንድንርቅ ሊያደርግ የሚያቅድ ነው፡፡
አንዳንዴ ፍርሀትን እንደ ስሜት እናስበዋለን፣ነገር ግን ብዙ ጊዜ መንፈስ ነው፡፡እንደውም ፍርሀት አንዱ የሰይጣን ምርጥ መሳሪያው ሲሆን በተለይ ክርስቲያኖችን በእርሱ መተንኮስ ይወዳል፡፡
ነገር ግን ኢየሱስ …ለሚያምን ሰው ሁሉም ነገር ይቻላል! (ማር.9፡23) ብሏል፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ የሚያምን የማይፈራ የተቀጣጠለ ክርስቲያን የጠላት ከፍተኛው ፍርሀቱ ነው!
እምነት የፍርሀት ተቃራኒው ነው ይባላል እናም እውነት ነው፡፡በእምነት እየኖርን መፍራት አንችልም፡፡ፍርሀት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃላት እንዳንቀበል ሽባ ያደርገናል፡፡እግዚአብሔር እንድናደርገው የጠራንን ወጥተን ከመታዘዝ ያከላክለናል፡፡
በእምነት ሀይል ፍርሀትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው ያለብን፡፡የግድ የእግዚአብሔርን ቃል በማወጅ እና ፍርሀት እንዲለቅ ማዘዝ ያስፈልጋል፡፡
ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ፍርሀት በራችሁን ሲያንኳኳ፣ እምነትን እንዲከፍት ላኩት!
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ የውሸት ማስረጃ እውነት መስሎ ቀርቦ ሲጋፈጠኝ አንቃኝ፡፡በአንተ እርዳታ በእምነት ሀይል ፍርሀትን በመጣ ቁጥር እያሯሯጥኩ መመለስ እንደምችል አውቃለሁ፡፡