የውጊያውን ሜዳ ለይ

የውጊያውን ሜዳ ለይ

የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፡፡ – 2 ቆሮ 10፡4

ሁል ጊዜ በውጊያ ላይ እንዳለን እናውቃለን? በዙሪያችን የሚታዩ መከራዎች ስንመለከት ዝምብሎ የሚከናወን ጦርነት ነው ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ እውነታው ግን ጦርነቱ ውስጣዊ ነው፡፡ የጦርነቱ ሜዳ በአእምሯችን ውስጥ ነው፡፡

የጦር ሜዳውን መለየት ሲያቅተን ጠላታችንንም በትክክሉ መለየት ያቅተናል፡፡ ችግራችን ሰዎች ናቸው፣ ገንዘብ ነው፣ ኃይማኖት፣ ሥርዓቱ ነው ብሎ የማመን አዝማሚያ እናሳያለን፡፡ አእምሯችንን እስካልታደሰ ድረስ የችግራችን ምንጮች እነዚህ ነገሮች ናቸው በሚለው እምነታችን ቀጥለን የተሳሳተ ውሳኔዎችን መወሰናችንን እንቀጥላለን፡፡

በየዕለቱ አእምሯችን ያለማቋረጥ በተለያዩ ሃሳቦች፣ ጥርጣሬዎች፣ ፍርሃቶች ይናጣል/ ይደበደባል፡፡ ከእነዚህ ነገሮች አንዱ ሽንፈትንና ንዴትን ሊያስከትሉ ይችላሉ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ላይ መተከል የእግዚአብሔርን ድልና ሃሴት ያመጣል፡፡

በሕይወትህ መቀደድ ያለበት አንዳንድ ዋና ምሽጎች ሊኖርህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ወግኖ የቆመ መሆኑን በማስታወስ አበረታታሃለሁ፡፡እየተካሄደ ያለ ጦርነት አለ ፤ የጦሩ ሜዳ ደግሞ የአንተ አእምሮ ነው፡፡ መልካሙ ዜና ግን እግዚአብሔር ከአንተ ወገን ሆኖ እየተዋጋ መሆኑ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፣ በእውነቱ በአእምሮዬ ውስጥ እውነተኛውን ጦርነት ችላ በማለት መታለል አልፈልግም ፡፡ መልካሙን ተጋድሎ እንድዋጋ ይጠብቀኝ ፡፡ ከጎኔ ስትሆን ማሸነፍ እችላለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon