በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። – 1 ጴጥ 5፡9
እግዚአብሔር ለአንተ ያለዉን ታላቅና ሀይለኛ ነገሮች ለማግኘት ከፈለግህ፤ ወደ አሉታዊ አስተሳሰብህ ስር ሂድና ተነጋገር፡፡ ምክንያቱም ስሩ እስኪነቀል ድረስ ክፉ ፍሬዎችን ማፍራታቸዉን አያቋርጡም፡፡
አብዛኛዉን ጊዜ ከባህርያችን በመነጩ ክፉ ፍሬዎች ጋር ስንነጋገር ጊዜ እናጠፋለን ነገር ግን የችግሩን ምንጭ ለማግኘት በጥልቅ አንቆፍርም፡፡ ክፉ ስር ለመንቀል ጥልቅ መቆፈር ያማል ነገር ግን ችግሮቻችንን ለማብቃት ብቸኛዉ መንገድ ይህ ነዉ፡፡ ወይ ትክክለኛ የሆነዉን ነገር በማድረግ እያመመን እንለወጣለን አሊያ ደግሞ ባለንበት ቦታ በመቅረት በዲያብሎስ ዕቅድ እየታመምን እንሰነብታለን፡፡ የእርሱ ዕቅድ ባሳለፍከው ህይወትህ ውስጥ ባለ አሮጌ ልምምዶች ላይ እንድትቆይ ነዉ፡፡
ጴጥሮስ ሚዛናዊ እንድንሆንና ዲያብሎስን እንድንቃወም ይመክረናል (1ጴጥ 5፡8-9 ተመልከት)፡፡ ወደ ክብር ህይወት የሚወስድህን አሊያም በአሮጌ ኑሮ የሚያሰቃይህን ህመም መምረጥ ግድ ይልሃል፡፡
እግዚአብሔር በህይወትህ ያለዉን ዕቅድ ለማግኘት ዛሬ ዲያብሎስን ተቃወም ፤ መንፈስ ቅዱስን ተከተል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! የዲያብሎስን ዕቅድ ለመቋቋም እርዳታህን እፈልጋለሁ፡፡ ክፉ ፍሬዎችን መቆፈር ከባድ እንደሆነ አዉቃለሁ ግን ወደ አንተ የሚያቀርበኝ ከሆነ ፈቃደኛ ነኝ፡፡ ዲያብሎስን ስቃዎምና አንተን ለመከተል ራሴን ሳስገዛ አጠንክረኝ፡፡