
ጥበብን የሚገኝ ሰው ምስጉን ነው፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፣ ምሣ 3÷13
ከእግዚአብሔር ለመስማት የእኔ ምርጫ የሆነው በጥበብ ቃልና በስሜት ሕዋሳቶች በኩል ነው፡፡ ጥበብ በሁኔታ ውስጥ እውነትን ሲገልጥ የስሜት ሕዋሳት ግን ጥሩ ውሳኔ በእውነታ ላይ ሆኖ ለመወሰን ይረዳል፡፡ ጥበብ መንፈሳዊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም ከሰው የምንማረው ስላይደለ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ ነው፡፡
ብዙ ጥልቅ የሆነ እውቀት ያላቸው ሰዎች ጥበብን የስሜት ሕዋሳትን ሚዛናዊነት ይጎድላቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል፡፡ ያዕ 1÷5
ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ለመሆን የስሜት ሕዋሳችን መጠቀም አለብን ሲሉ ሲሰማ በጣም ይገርመኛል፡፡ መንፈሳዊ ሰው ቀኑን ሙሉ በመንፈሳዊ የክብር ደመና ውስጥ እየተንሳፈፈ ብቻ የሚኖር ሳይሆን በገሃዱ ዓለም በግልፅ ሁኔታዎች በቀጥታ መንገድ ነው፡፡ እነዚህም ጉዳዮች ግልፅና ትክክለኛ እውነታውን እንደማንኛውም ሰው መልስ የሚፈልጉ ሲሆን መልሱም የሚገኘው በእግዚአብሔር ቃል ሲሆን የሚበራልን በመንፈሱ በኩል ነው፡፡
እኛ በበኩላችን የመፈለግ ድርሻችንን ስንወጣ እግዚአብሔርም የመናገሩን ድርሻ ይወጣል፡፡ ነገር ግን እርሱ የጥበብ መንፈስ ስለሆነ ጥበብ የጎደለውን ነገር ወይም መንገድ አይነግረንም፡፡ ብዙውን ጊዜ እግዚብሔር አንዲነግረንና እንዲመራን እንጠይቃለን፡፡ ነገር ግን እርሱ ግልፅ የሆነ ከቃሉ ካልሰጠን ወይም በልባችን ቃል ካላመጣ በእርጋታ ምንም እርምጃ ሳንወስድ የእለት ተግባራችን በመፈፀም ማረጋገጥ አለብን፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱን ጥቃቅን ምርጫና ውሳኔዎቻችን ላይ በሥልጣን የሚያዝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ጥበብ ሰጥቶን የስሜት ሕዋሳችንን ሚዛናዊ ውሳኔ በማንቃት በሁለቱ ጥምረት ውጤታማ ውሳኔ እንድናደርግ ይረዳናል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በድርሻህ እግዚአብሔርን ከፈለክ የድርሻውን ይናገርሃል፡፡