የጥበብ ቃል

የጥበብ ቃል

ለአንዱ ጥበብን መናገር ይሰጠዋልና፡፡ 1 ቆሮ 12÷8

1ኛ ቆሮ 1÷30 ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተደረገልን ‹‹ጥበባችን›› ነው ይላል፡፡

እንዲሁም የመክብብ መጽሐፍ ፀሐፊ በተደጋጋሚ የሚነግረን ጥበብን እንድንፈልግና ማግኘት እንደምንችል ነው፡፡ ጥበብ ለሁሉም ሰዎች መገኘት የሚችል ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹የጥበብ ቃል›› የተለየ ዓይነት ሲሆን ማንም ሰው ሊኖረው የሚገባው አይደለም፡፡ ሁሉም ጥበብ ከእግዚአብሔር ነው፡፡ ሌላውም ጥበብ ከልምድና ትምህርት በመከታተል የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የዛሬው ጥቅስ የሚዘረዘረው የጥበብ ቃል ዓይነት ጥበብ አይደለም፡፡ የጥበብ ቃል ይዘት መንፈሳዊ መመሪያ ያለው ነው፡፡ በሥራ ላይ በምውልበት ጊዜ ግለሰቡ በመንፈስ ቅዱስ በመለኮታዊ ኃይል የምሠራውም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በተለየ መልኩ እንዴት አድርጎ ማስኬድ እንዳለበት የብልሃት መንገድ ያስፈልገዋል፡፡ ያ ደግሞ ከተፈጥሮአዊ ትምህርት ወይም ልምምድ የሆነን ከእግዚአብሔር ዓላማ በሆነበት መንገድ ነው፡፡

እኛ ብዙውን ጊዜ በዚህ ፀጋ በተከታታይ እንሰራበታለን፡፡ እንዲያውም ስለነገሩ በማናቅበት ሁኔታ ሁሉ ፀጋው ይሰራል፡፡ ለሆነ ሰው ተራ የሚመስለው ነገር ልንለው እንችላለን፡፡ ነገር ግን ለአድማጩ ድንቅ የሆነ የጥበብ ቃል ነው፡፡

የጥበብን ቃል ስለሚናገሩት ነገር ምንም ፍንጭ ከሌላቸው ልጆች ተቀብየየ አውቃለሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የእኔን ትኩረት ለመያዝ ይፈልግ ስለነበር እኔ የእርሱ ንግግር መሆኑን የማውቅበትን ምንጮች ተጠቅሞ ይናገረኛል፡፡ የእግዝአብሔርን ምሪት በጥበብ ቃላት በመጠየቅ ተጠባብቀው፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ጥበብን እሻ ምክንያቱም በጊዜው የተነገረ የጥበብ ቃል ሕይወት ለዋጭ ስለሆነ ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon