እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው፡፡ – ኤፌ 3፡19
እግዚአብሔር ካለፈ ጉዳታችሁ ሲፈውሳችሁ ሊረዳችሁ ብቻ አይደለም የሚፈልገው ነገር ግን ልምዳችሁ ለሌሎች ተመሳሳይ ፈውስን የሚለማመዱበት ማምለጫ እንዲሆናቸው ነው የሚፈልገው፡፡
ቀስ በቀስ እግዚአብሔር እኔን እና ዴቭን ወላጆቼን ወደ ሴንት ሉዊስ እንድናመጣቸው እና ቤት እንድንገዛላቸው ሲመራን ለእኔ በጣም ከባድ ነበር፡፡በመጨረሻ ግን አባቴ ላደረገብኝ ነገር ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ጌታን ተቀበለ፡፡
በይቅርታ ውስጥ ባለው ሀይል እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ እና ተሀድሶዬን ደግሞ አባቴን ለመፈወስ እንዲጠቀምበት ስለፈቀድኩለት ሙሉ ለሙሉ አዲስ የሆነ ጤናማ ስሜት መለማመድ ጀመርኩ፡፡
እኛ ሁላችን በብዙ መንገድ ልንጎዳ እንችላለን፡፡ ብቸኝነት፣ተስፋ መቁረጥ፣ፍርሀት እና ደህንነት ያለመሰማት ስሜት ጥልቅ በሆነ መንገድ እኛን የመጉዳት ችሎታ አላቸው፡፡የእግዚአብሔርን ፍቅር ተቀብዬ እስክለማመድ ድረስ እና ሁሉን ነገር እንዲቀያይረው እስክፈቅድለት ድረስ ባለፈው ህይወቴ ከተጎዳሁት ጉዳት ላይ ፈቀቅ ማለት አልቻልኩም ነበር፡፡
ከህመማችሁ በላይ አልፋችሁ ከመሄዳችሁና ሌሎችን መውደድንና ይቅር ማለትን ከመማራችሁ በፊት የእግዚአብሔርን ፍቅር መለማመድ አለባችሁ፡፡
የኋላ ታሪካችሁን ስታስቡ ሁሌም እግዚአብሔር ጥልቅ በሆነ መንገድ እንደሚወዳችሁ አስታውሱ፡፡መጽሀፍ ቅዱስ ሙሉ የምንሆነው እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ልንረዳው የማትችለውን የክርስቶስን ፍቅር ስንለማመድ እንደሆነ ይናገራል፡፡ፍቅሩን ስትቀበሉ በልባችሁ ውስጥ ፈውስ ይጀምርና በእርሱ ህይወት ሙላት እናንተም ሙሉ ትሆናላችሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ የኋላ ታሪኬ ውስጥ ያለውን ህመም እና ጉዳት ማሸነፍ እንድችል ረድተኸኝ ፈውሴን ሌሎችን ለመርዳት ትጠቀምበታለህ ብዬ አምናለሁ፡፡የክርስቶስን ፍቅር አለማምደህ በአንተ ህይወት ሙላትና ሀይል ሙሉ አድርገኝ፡፡