ያለፈ ውጤታማነትን ማስታወስ

ያለፈ ውጤታማነትን ማስታወስ

ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ እግዚአብሔር አሁንም ከዚህ ፍልስጤማዊ እጅ ያድነኛል፡፡ሳኦልም “ሂድ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን “አለው፡፡ – 1 ኛ ሳሙ 17:37

እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስንገባ የምናስበው አሉታዊ በሆነ መልኩ ነው፡፡ነገር ግን አስቸጋሪ ጊዜዎችን ለማሳለፍ አሉታዊ ሃሳቦቻችሁን አውጥታችሁ በመጣል በአዎንታዊ ሀሳቦች ልትተኩዋቸው ይገባል፡፡

እግዚአብሔር ቃሉን በማጥናት ውስጥ አስደናቂ ውጤት በሚያስገኝ “በእውነት ጎዳና” ሊወስዳችሁ ይፈልጋል፡፡አሉታዊ ሀሳቦቻችሁን አጽድታችሁ ባላችሁበት ሁኔታ ውስጥ ያለውን አዎንታዊ ነገር እንድታዩ ይረዳችኋል፡፡

አዎንታዊ መሆን ሀያል ነገር ነው፡፡አዎንታዊ ለመሆን አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ነገር ደግሞ የትናንትና ውጤታማነታችሁን ራሳችሁን ማስታወስ ነው፡፡

ዳዊት ግዙፉን ጎሊያድን ሲገጥም ያሸነፋቸውን አንበሳ እና ድብ አስታውሶ አሁን ላለበት ሁኔታ ድፍረትነ አገኘ፡፡

አሁን እያለፋችሁበት ያለው ሁኔታ አስቸጋሪ ከሆነ ይሄ ያጋጠማችሁ የመጀመሪያው ችግር እንዳልሆነ ላስታውሳችሁ፡፡ያለፈውን አልፋችሁታል (ምናልባትም በጣም ጠቃሚ ትምህርቶችንም ተምራችሁበታል) ይህኛውንም ታልፉታላችሁ፡፡

ልክ እንደ ዳዊት ያለፉትን ውጤታማነቶቻችሁን አስታውሱ፡፡ከዛ ወደቃሉ ሂዱና እግዚአብሔር የሚለውን እዩ፡፡የተሸሉ ቀናት እየመጡ ናቸው፡፡እግዚአብሔር ተስፋ ሰጥቶናል!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አንዳንዴ ከፊቴ ያለው ነገር የማይቻል ይመስላል ነገር ግን ባለፈው ህይወቴ ውስጥ አስቸጋሪ ጊዜዎችን አሳልፈኸኛል አሁንም ልታደርገው እንደምትችል አውቃለሁ፡፡ያለፈውን ውጤታማነቴን እንዳስታውስ እና ስላለሁበት ሁኔታ አዎንታዊ በሆነ መልኩ እንዳስብ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon