ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ። – 1 ኛጢሞ 1፡16
የትዳር ባላጋራችን የጎዳንን ያህል ለመጉዳት የምናስብ ከሆነ ትዳር እጅግ በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው በተከፋችሁበት ጊዜ አዕምሯችሁን ክፍት እና ግልጸ ማድረግ ከባድ ሊሆን ይችላል ፣ የምናፈቅረው ሰው ሊጎዳን አይችልም ብለንም እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ እንዲያውም ለመጎዳት ፈቃደኛ ሳትሆኑ በእውነት ሌላን ሰው መውደድ አትችሉም።
እውነተኛ ፍቀር ምህረትና ይቅርታን ያደርጋል፡፡ ፍቅር ለሌላው ሰወ ዕድልን በመስጠት ያምናል። ፍቅር ሌላው ባለንጀራችንን ወይም አጋራችንን በማመን ላይ ተመሰረተ ነው ፤ በሚቀጥለው ጊዜ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋሉ ብሎ ያምናል ፤ ለነርሱ መልካም ነገርም ይመኛል፡፡
በትዳራችሁ ውስጥ ከምታደርጓቸው የየዕለት ግንኙነት የተነሳ ጥልቅ የሆነ መጎዳት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ነገርግን ያበሳጫችሁን ነገር ለመተው ውሳኔ ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡ በእውነት ይቅር ለማለት ፅጋ እና ብርታት ይሆናችሁ ዘንድ ለእግዚያብሔር ፅልዩ ፣ በእርሱም ላይ ተደገፉ።
በትዳራችሁ ውስጥ ይቅርታ ማድረግ እየከበዳችሁ ከመጣ ይህ ምሬት ከየት እንደመጣ እግዚያብሔር እንዲያሳያችሁ ጠይቁት። ለእናንተ ምን እንደሚገልጥላችሁ ስታዬ በጣም ልትገረሙ ትችላላችሁ፡፡ ነግርግን እውነቱን ስትረዱ መጎዳታችሁንና ምሬታችሁን ትታችሁ ይቅርታ ለማድረግ መዘጋጀት አለባችሁ፡፡ለትዳር አጋራችሁ ይቅርታ ለማድረግ ወስኑ በትዕግስትም ከእነሱ ጋር ተመላለሱ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
ጌታሆይ ትዳሬ የተሻለ ፣ ውጤታማና ጥሩ እንዲሆን እሻለሁ፡፡ በህይወቴ ውስጥ ያሉትን ይቅርታ ማድረግ የተሳነኝን ሁኔታዎች ሁሉ ማሸነፍ እንድችል እርዳኝ፡፡ የትዳር አጋሬንም አንተ እንደምትፈልገው እንድወዳት እርዳኝ፡፡