ይቅርታ፡ዲያብሎስን ወደ ህይወታችሁ እንዳይገባ ማድረጊያው ቁልፍ

ይቅርታ፡ዲያብሎስን ወደ ህይወታችሁ እንዳይገባ ማድረጊያው ቁልፍ

እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤በእርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለእናንተ ስል ሰው፡፡ይህንንም የምናደርገው ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኝ ነው፤የእርሱን እቅድ አንስተውምና፡፡ – 2 ኛ ቆሮ 2፡10-11

ይቅርታ በጣም ይረዳናል ምክንያቱም እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ እንዲሰራ ይለቀዋል፡፡ይቅር ባለማለት መርዝ ሳልሞላ ስቀር ደስተኛ እሆንና የተሻለ አካላዊ ጤንነት ይሰማኛል፡፡ መራርነት ፣ አለመተውና ይቅር አለማለት ሰው ላይ ከሚያመጡበት ጭንቀት እና ጫና የተነሳ ከባባድ በሽታዎች ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡

ሌሎች ሰዎችን ይቅር ካላልን አብ ሀጢያታችንን ይቅር አይለንም ስለዚህም የዘራነውን እናጭዳለን (ማቴ.6፡14-15ገላ.6፡7-8ን ይመልከቱ)፡፡ምህረትን ዝሩና ምህረትን እጨዱ ፤ ፍርድን ዝሩና ፍርድን እጨዱ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ በእግዚአብሔር ጸጋ ይቅር ማለትና የልባችሁን በር ለጌታ ክፍት ማድረግ አለባችሁ፡፡

ይቅር አለማለት ለዲያብሎስ ምሽግ ለመፍጠር የሚያስፈልገውን የእግር ማስገቢያ ይሰጠዋል፡፡ምሽግ ሲሰራ የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖ መቋቋም ይችላል፡፡ይቅር ስትሉ ጠላት በእናንተ ላይ ጥቅም እንዳያገኝ ይከለከልና ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ህብረት በደንብ እንዲሳለጥ ያደርጋል፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል ለመታዘዝ ስትመርጡ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በጠላት ላይ ድልን ልታገኙ ትላላችሁ፡፡ስለዚህ ፈጥናችሁ ይቅር በማለት ለእራሳችሁ ውለታን ዋሉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ለሰይጣን እግሩን ማስገቢያ ወይም ምሽግን መስሪያ ልሰጠው አልፈልግም፡፡ከአንተ ጋር ባለኝ ህብረት ምንም ነገር በመንገዴ እንዲገባ አልፈልግም፡፡ከአንተ ጋር በነጻነት ህብረትን አደርግ ዘንድ ይቅርታ ማድረግን እመርጣለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon