ደስተኛ ልትሆን ተፈጥረሃል

ደስተኛ ልትሆን ተፈጥረሃል

ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት፣ በሥራውም ከመርካት ሌላ የሚሻለው ነገር የለውም፤ ይህም ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደሚሰጥ አየሁ፤ ይህ እንኳ በእግዚአብሄር እጅ ነው ፡፡ – መክብብ 2፡24

ደስታ ማለት ማጠናቀቅ ያለብንን ሩጫ አሊያም ተግባር ለማከናወንና ለማጠናቀቅ የሚያግዘን ኃይል ሰጪ ነገር ማለት ነው፡፡ በክንውናችን መካከል የድካም ስሜት ተሰምቶን ውስጣችን በምሬት ከተሞላ አንድ ቦታ ላይ ልናቆም እንችላለን ዳሩ ግን ላለማቆም ደስተኛ መሆን ስንጀምር የመቀጠል ኃይል በውስጣችን ይሆናል፡፡

በጣም ብዙ ሰዎች ስራ ቸውን በተገቢው ይሰሩና ሲደክማቸው ይሰላቻሉ ይሁንና እግዚያብሔር በስራችን እንድንደሰት መፍቀዱን ባለማወቃቸው በቁጭት ይሞላሉ፡፡ መስራት እንዳለብን እግዚያብሔር እንዳዘዘን ሁሉ እንድንደሰትም አዟል፡፡መክብብ የሚነግረን በስራችን መካከል መደሰትና መርካት እንዳለብን ነው፡፡

ሰይጣን አዕምሯችንን አስሮታል ምክንያቱም በስራችን በድካም ብቻ እንድንሆን በማድረግ በጣም ስልቹ እንድንሆን በማድረግ እየተሳካለት ነው፡፡

በስራችን ላይ ከግብ ለመድረስ የምንታትረውን ያህል ማረፍና መደሰት እንዲሁም መርካት ይኖርብናል፡፡እግዚያብሔር በሰጣችሁ ስራ ላይ በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት ይኖርባችኋል እንዲሁም ደግሞ ለራሳችሁ ተገቢውን እውቅና በመስጠት ማረፍና መደሰት በስራችሁም ለውጥ መርካት አለባችሁ፡፡ እግዚያብሔር ይህ እንደሚገባችሁ ያስባል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ በሰጠኸኝ ህይወት ደስተኛና ህይወትንም ልደሰትባት እሻለሁ። በትጋት እንድሰራና በዚውም ልክ ደግሞ ተገቢውነ እረፍት እንዳደርግና እድደሰት መንገድህን አሳየኝ፤ በክርስቶስ ስለሰጠህኝ የሚበዛ ህይወት አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon