ደስታውን ማግኘት

ደስታውን ማግኘት

ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሀኒት ነው፤የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል፡፡ – ምሳሌ 17፡22

ስቂኝ ታሪክ መስማት ትፈልጋላችሁ? በመደበኛ የየዕለት ተዕለት ህይወቴ ከሚያጋጥሙኝ ነገሮች ውስጥ የወጡ እንደዚህ ያለ ብዙ ታሪኮች አውቃለሁ  ፡፡ታሪኮቹ ሲፈጸሙ እየሳቅኩ አልነበረም ነገር ግን ዛሬ በጉዳዩ ላይ መሳቅ ሰለቻልሁ ደስተኛ ነኝ፡፡

ጸጉሬ ሲንጨበረር አስቂኝ ነገር ነው ብዬ አላምንም ነገር ግን ያደረግኩትን ብታዩ እናንተ ትስቃላችሁ፡፡ልብስ ስሰፋ በተለይ ለሚለብሱት ሰዎች አስደሳች አልነበረም፡፡ግሮሰሪ ውስጥ ዴቭ ሶፍት ሲወረውርብኝ በጣም ነበር የሚደብረኝ፡፡አሁን ግን ምንም እያደረገ ቢሆን ጥቂት መደሰትን እንደሚያውቅበት ገብቶኛል፡፡እንደዚህ ያሉ ጊዜዎችን ሳስታውስ እንዴት አዝናኝ ነገር ውስጣቸው እንደነበር እያሰብኩ እደሰታለሁ፡፡

አሁን በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙን ነገሮች ሁሉ አዝናኝ እንዳልሆኑ አውቄያለሁ ቢሆንም ግን ሁላችንም በህይወታችን የበለጠ መዝናናት እንዳለብን ተረድቻለሁ፡፡ጊዜ ወስዳችሁ ብታስቡ በየቀኑ አሁን ላይ የሚያስቃችሁ እና ወደ ህይወታችሁ ደስታ የሚያመጣ ነገር እንደማይጠፋ እወራረዳለሁ፡፡

እግዚአብሔር ልጆቹ በተወሰነ መልኩ እንዲዝናኑ ይፈልጋል፡፡መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሀኒት ነው ይላል፡፡እኛ ሁላችን ጤነኛ መጠን ያለው ሳቅ በየቀኑ በርከት ያለ ጊዜ ያስፈልገናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ደሰታ ከመጠን ማለፍ አይችልም!

በእያንዳንዱ ቀን ስራዬ ብላችሁ ፈገግ የሚያስብላችሁን ወይም የሚያስቃችሁን ነገር እንድትፈልጉ አበረታታችኋለሁ…እናም ለሌላም ሰው ፈገግታችሁን እና ሳቃችሁን በማካፈል ቀኑን ማብራታችሁን እርግጠኛ ሁኑ!


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ቃልህ ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሀኒት ነው ይላል፡፡በህይወት ውስጥ ያለውን ደስታ እና አዝናኝ ነገር እንዳገኝ ስለምትረዳኝ አመሰግናለሁ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon