ኃጥዕ ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፣ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ያለ ፍርሃት ይኖራል፡፡ ምሳ 28 1
አንዱና ዋነኛ ሰዎች የማይፀልዩበትና የሚፈልጉትንና የሚያስፈልጋቸው ነገር ለመጠየቅ ግትር የሚሆኑበት ምክንያት ዋጋ ያለው ስለማይመስላቸው ነው፡፡ እነርሱ ስለ እራሳቸውም መልካም ነገር አይሰማቸውም፡፡ መንፈሳዊ ብቃት ያላቸውና ጉድለት ስለማይሰማቸው ነው፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር ፀሎታቸውን የሚሰማቸው ስለማይመስላቸው ነው፡፡ እኛ ሁላችን እንሳሳታለን፡፡ ስለዚህም ስህተት ስንሰራ የእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ መቀበል ያስፈልገናል፡፡ ያ ስህተታችን በይቅርታ ሲወገድ የእግዚአብሔር በረከት ወደ ሕይወታችን እንዲፈስ መንገድ ይከፍታል፡፡
ወደ እግዚአብሔር ቀርበን በፀሎት ስንጠይቀው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በተገኘልን ጻድቅ መሠረት ያገኘነውን የእግዚአብሔር የልጅነት ሥልጣን (የወንድና የሴት ልጅነት ሥልጣን) በመረዳት መሆን አለብን፡፡ አለበለዚያ የእርሱን ድምፅ በግልፅ ወይም የእርሱን የፀሎታችን መልስ በትክክል ላንሰማ እንችላለን፡፡ እንደምትመለከተው ብዙውን ጊዜ የእኛ ጽድቅ የተመሠረተው እኛ በምናደርጋቸው ትክክለኛ ነገሮች ወይም አመለካከቶች ላይ ይመስለናል፡፡ እውነታው ግን እኛ በራሳችን እራሳችንን ማጽደቅ አንችልም፡፡ እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ ጽድቅ እኛ በምናደርገው ትክክለኛ ነገር ላይ አይመሠረትም፡፡ ነገር ግን የተመሠረተው ኢየሱስ ለእኛ ባደረገው ላይ ነው፡፡ የእርሱ ጽድቅ በእምነት ለእኛ ይሆናል፡፡ አንዴ ያንን ካመንን ከዚያ በሂደት ወደ ትክክለኛ እግዚአብሔር ፀሎታችንን የምመልሰው እርሱ መልካም ስለሆነ ሁልጊዜ ማስታወስ አለብን እንጂ ከሆነው አንፃር አይደለም፡፡ በፀሎታችን በድፍረት በመቅረብ ሁሌም እንደሚሰማን መተማመን አለብን፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔርን በመታመን በድፍረት ብትፀልይ ስህተታችሁን ወደ ተዓምር ይቀይረዋል፡፡