
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። – ፊል 4፡4
ድብርት በከፊል እንዲህ ይተረጎማል “ባዶነት፣ በወረደ ስሜት ዉስጥ መገኘት፣ የሐዘን ድባብ፣ ተስፋ መቁረጥ” ድብርትን የሚያመጣ አንዱ የተለመደ ነገር የእኛ ሁኔታ ሳይሆን ስላለንበት ሁኔታ የሚሰማን አመለካከት ነዉ፡፡ ለዚህ ነዉ ዲያብሎስ አንተ ዋጋ እንደሌለህና እንደተወገዝክ እንድታስብ ሊያደርግህ የሚፈልገዉ፡፡
ነገር ግን አንተ ዲያብሎስ እንዲጫንህ ካልፈቀድህ፤ አያጠቃህም፤ ካላጠቃህ ደግሞ ድበርት ውስጥ ሊያስገባህ አይችልም፡፡
እኔ እንደማስበዉ ድያብሎስን ለመቋቋም፣ ድልን ለመቀዳጀትና ከድበርት ነጻ ለመዉጣት ጥሩዉ መንገድ መንፈስ ቅዱስ ወደ ደስታ መንገድ እንዲመራህ መፍቀድ ነዉ፡፡ ጠላት የሚፈልገዉ በአሉታዊዉ ነገር ላይ እንድናተኩር ሲሆን፤ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በአዉንታዊዉ ነገር እንድናተኩር ይፈልጋል፡፡
ፊል 4፡4 ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ይላል፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ስናተኩር፣ በእርሱ ስንደሰት ድበርት በዉስጣችን ቦታ ያጣል፡፡ ስለዚህ በሚቀጥለዉ ጊዜ ጠላት ዝቅተኛ ወይም ሀዘንተኛነትን እንድታስብ ሊያደርግህ ሲሞክር በጌታ መደሰትን ምረጥ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ታላቅና አስደናቂ ነህ ስለዚህ ሁል ጊዜ በአንተ መደሰት እችላለሁ፣ ድበርት በዉስጤ ቦታ አይኖረዉም ምክንያቱም በአንተ ተሞልቻለሁና፡፡