
እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይኖራል፣ ሰው ግን አያስተውልም፡፡ ኢዮ 33 14
እኛ ስለተለያዩ ጉዳዮች በየቀኑ ከእግዚአብሔር መስማት እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን በሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆኑ ወቅቶች በተለያየ መልክ በግልፅ ድምፁን ለመስማትና ለማወቅ የምንፈልግበት ሁኔታዎች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ሊናገረን ይፈልጋል፡፡ እኛ ግን ዝግ አእምሮን በሕይወታችን በማሳደግ የእርሱን የመናገሪያ መንገድ ለመገደብ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ከእንግዲህ እንዲህ ማለት የለብንም፡-
‹‹እግዚአብሔር በቃሉ ብቻ እንዲናገረኝ እንጂ በሕልም እንዲናገረኝ አልፈልግም፡፡›› ‹‹እግዚአብሔር በመጋቢዬ በኩል እንዲናገረኝ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን በጓደኞቼ በኩል እንዲናገረኝ አልፈልግም፡፡›› ማለት የለብኝም፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ከሚናገርባቸው መንገዶች የፈለገውን መንገድ መርቶ ሊናገረን ይችላል፡፡ ነገር ግን የትኛውንም መንገድ ብመርጥ ችግር የለውም፡፡ እኛ ሁሉንም ለእርሱ በመተው ተስፋውን እንዲፈፅም መፍቀድ አለብን፡፡
የሰማነው ድምፅ ከእግዚአብሔር ወይም ከእራሳችን አእምሮ ወይም ስሜት መስማታችንን መለየት ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር መስማትን ለመማር ዓመታት ፈጅቶብናል ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ የሆነው ግልፅ የሆነ ትምህርት እግዚአብሔር እንዴት ከሕዝቡ ጋር ሕብረት እንደሚያደርግ በበቂ ካለማግኘት ነው፡፡ እግዚአብሔር እርሱ እኛን እንደ ጥሩ እረኛ ሊመራን እንደሚፈልግ እንድናውቅ ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር በብዙ መንገድ ይናገራል፡፡ ስለዚህ ዛሬ እንዲናገርህና በፈለገው መንገድ እንዲመራህ ፍቀድለት፡፡ አንድ ወቅት እግዚአብሔር በአህያ በኩል ለነብዩ ተናግሮአል፡፡ ስለዚህ እርሱ በመረጠው መንገድ ሲናገር ለመስማት የተከፈተ አእምሮ ሊኖረን ይገባል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር እንዴትም አድርጎ ለሚናገርህ ጉዳይ የተከፈተ አእምሮ ይኑርህ፡፡