ጉልበት ያለዉ ፀሎት

ጉልበት ያለዉ ፀሎት

ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግማችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፣ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ (ማቴ 5፡44)

ጉልበት ካላቸዉ ፀሎቶችህመካከል አንዱንለጠላቶችህመፀለይ ትችላለህ፡፡ የፀሎት ጉልበት ያለዉን ኃይለኛ ሰዉ ለመመልከት ከፈለግህ፣ ለጠላቶቹ የሚማልድ ሰዉ እንደሆነ መገንዘብ አለብህ፡፡ ለካዱንና ላስቆጡን ሰዎች ስንፀልይ እግዚአብሄር እብዝቶ እንደሚባርከን አምናለሁ፡፡

እዮብን ታስታዉሳላችሁ? ወዳጆቹ ከጎዱትና ተስፋ ካስቆረጡት በኋላ ለእነሱ መፀለይ ነበረበት፡፡ ነገር ግን ወዲያዉ ከፀለየ በኋላ እግዚአብሔር ህይወቱን ማደስ ጀመረ፡፡በአርግጥም እግዚአብሔር እዮብ ያጣቸዉን ነገሮች ሁሉ እጥፍ አድረጎ መለሰለት፡፡ (ኢዮብ 42፡10 ን ተመልከቱ)! ለጎዱን ሰዎች የምንፀልየዉ ፀሎት በጣም ጉልበት ያለዉ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ይህንን ባደረግን ጊዜ ከዚያ ሰዉ ጋር በፍቅር አንመላለሳለን፣ የእግዚአብሄርንም ቃል እንታዘዛለን፡፡

ዛሬ ከተካፈልነዉ ቃልየእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት እንችላለን፡፡ ከዚህ መልእከት ጌታ ኢየሱስ ምን ያስተምረሃል? ለጠላቶቻችን እንድንፀልይ ያዘናል፡፡ ባልተገባ መንገድ ተጠቅመዉብኛል፣ጭካኔ የተሞላዉ ነገር አድረገዉብኛል፣ በደል ፈፅመዉብኛል፣ ፀያፍ ነገር ተናግረዉኛል የምትሏቸዉን ሰዎች ሁሉ ባርካቸዉ እንጂ አትርገማቸዉ፡፡ ፀልይላቸዉ፡፡ እግዚአብሔርም ጠላትን መባረክ ቀላል እንዳልሆነና ያንን ማድረግ ለናንተ ባጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ያዉቃል፡፡ አስቸጋሪ እንደሆነ ብታዉቀዉም እንኳ ለእግዚአብሄር ስትልአድርገዉ፡፡ በመንፈሳዊዉ አለም ጠላቶቻችንን ከመርገም ይልቅ ለመፀለይና ለመባረክ መወሰን ባጣም ትልቅ ጉልበት አለዉ፤ ከዚህ የተነሳም እግዚአብሔር በህይወታችን ታላቅ ነገርን ያደርጋል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ክፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ክፋት እናንተም እንድታደርጉ ገፋፍተዉ ወደ ራሳቸዉ ደረጃ ዝቅ እንዲያደርጓችሁ ቢሞክሩም እናንተ ግን አትፍቀዱላቸዉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon