ጊዜያችሁን በአግባቡ መጠቀም

ጊዜያችሁን በአግባቡ መጠቀም

እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች (እንደሚያገናዝብ እና እንደ ባለ አዕምሮ ሰዎች) እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ፡፡ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ (እያንዳንዱን መልካም ዕድል መጠቀም)፡፡ – ኤፌ 5፡15-16

ጊዜ እውነትም ይበራል፣አይደል? በሌላ በኩል ደግሞ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ጊዜ ዳዴ የሚል ነው የሚመስለው!ጊዜ የሚሄደው በፍጥነትም ይሁን በዝግታ እያንዳንዳችን በምድር ላይ ያለን ቆይታ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ይሄንን በአዕምሯችን ይዘን በጊዜያችሁ ምን እያደረጋችሁ ነው? ብዬ ልጠይቃችሁ እፈልጋለሁ፡፡

ጊዜ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው! በየቀኑ እንዴት ጊዜውን ወስዶ የሚፈልገውን አይነት ሰዎች እንድንሆን አድርጎ እንደሰራን አያለሁ፡፡ከዛም መልካምነቱን እንድንለማመድ በምህረቱ እና በጸጋው በህይወታችን እየሰራ ካለው ነገር ጋር የምንስማማበትን ጊዜን ሰጠን፡፡

ስለዚህ ራሳችሁን ጠይቁ፣እግዚአብሔር በእኔ እየሰራው ካለው ነገር ጋር ተስማምቻለሁ? ወይስ በራሴ መንገድ ነገሮችን ለመስራት እየታገልኩ እና እየተዋጋሁ ነው?

ከእግዚአብሔር ጋር እየታገላችሁ ካላችሁ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ጊዜያችሁን እያባከናችሁ እንደሆነ ነው፤ነገር ግን ከእርሱ ጋር እየተስማማችሁ ከሆነ ጊዜያችሁን ለታላላቅ ነገሮች እየተጠቀማችሁበት ነው፡፡

አስታውሱ፣እግዚአብሔር ቸር ነው ፡፡የራሱን ጊዜ ይወስዳል፡፡በእኛ እየሰራ ካለው ስራው ጋር እንድንስማማ በመልካምነቱ ሲጠብቀን እኛ ግን ረጅም ጊዜ እየወሰደ እንዳለ ልናስብ እንችላለን፡፡እርሱ አይቸኩልም፡፡ትዕግስተኛ ነው፡፡የእኛ ትግል የሚያዘገየው መሻሻላችንን ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ ምናልባት ይሄን አመለካከታችሁን ለመለወጥ እና ነገሮችን ማከናወኛ አዳዲስ መንገዶችን ለወደፊቱ ለመፈለግ..ለህይወታችሁ አዲስ ራዕይን ለመያዝ…በእኛ ውስጥ ያለማቋረጥ ለእኛ ጥቅም በስራ ላይ ባለው በእርሱ ላይ እምነታችሁን እና መታመናችሁን ለማደስ ጥሩ ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡

እኔ የማበረታታችሁ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ እና ጊዜያችሁን በህይወታችሁ እየሰራው ካለው ነገር ጋር በስምምነት እንድታሳልፉ ነው፡፡አላማችሁን እርሱ እንዲተረጉመው ፍቀዱለት፡፡ምንም ያህል ጊዜ ቢፈጅ እንኳ ለእናንተ ታላላቅ እቅዶች እንዳሉት፣እንደሚወዳችሁ እና በልቡ ሁልጊዜ ለእናንተ የሚበጀውን እንደሚስብ እወቁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ጊዜዬን ከአንተ ጋር በመጣላት ማሳለፍ አልፈልግም፡፡በእኔ ከምትፈጽመው ታላቅ ስራህ ጋር በመስማማት ጊዜዬን ማሳለፍ እፈልጋለሁ፡፡ጊዜዬን ማቃጠል ስጀምር እንደምትወደኝ እና የአንተ ጊዜ ሁሌም ምርጡ እንደሆነ ስለምታስታውሰኝ አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon