ጊዜ ውሰድ፣ ጊዜ ፍጠር

ጊዜ ውሰድ፣ ጊዜ ፍጠር

ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ አስብ። (ኢዮብ 37፡14)

ብዙ ሰዎች “እግዚአብሔር በፍጹም አይናገረኝም” ሲሉ ሰምቻለሁ። ነገር ግን እነርሱ እርሱን በፍጹም እንደማይሰሙት፣ ከእርሱ እንዴት እንደሚሰሙ እንደማያውቁ ወይም ለድምፁን ለማወቅ እንደተሳናቸው የበለጠ እርግጠኛ ነኝ። እግዚአብሔር በቃሉ፣ በተፈጥሮ ምልክቶች፣ ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ መገለጦች እና በውስጣዊ ማረጋገጫ ለእኛ ለመናገር ብዙ ሙከራዎችን ያደርጋል። እነዚህ ሁሉ በዚህ የጥሞና ጊዜ ማስታወሻ ውስጥ የጻፍኳቸውን ናቸው።

አንዳንድ ጊዜ በልባችን ውስጥ ወይም በሕይወታችን ውስጥ እርሱን በግልጽ ከመስማት የሚያግዱን የተወሰኑ መሰናክሎች ስላሉ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት የማንችል ይመስለናል። ከነዚህ ነገሮች አንዱ በቀላሉ በጣም በስራ መወጠር ነው። በጣም ከመጠመዳችን የተነሳ እግዚአብሔርን ለመጠበቅ ወይም ድምፁን ለመስማት ጊዜ የለንም። እንደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ሌሎችን በማገልገል በመሳሰሉ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በጣም ተጠምደን ሊሆን ይችላል ባለን የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ግን ለእግዚአብሔር ቦታ አይኖረንም። ለእግዚአብሔር በጣም የሰራሁበትን ጊዜ ነገር ግን ከእሱ ጋር ለማሳለፍ ጊዜ ሳይኖረኝ የቀረበትን ጊዜ ማስታወስ እችላልለሁ፤ ይህ በብዙ ሰዎች ላይ ይከሰታል።

ለእግዚአብሔር የምናደርገው ነገር ሁል ጊዜ ከእሱ ጋር ካለን የግል ግንኙነት ሁለተኛ መሆን አለበት። ጊዜ እንደወደድነው የምንሰራበት የራሳችን ስለሆነ የምንሰራውን በጥበብ መምረጥ አለብን። እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ ተመሳሳይ የጊዜ መጠን ያለው ሲሆን አንዴ ከተጠቀምንበት መመለስ አንችልም። በእንተ እቅድ ውስጥ እግዚአብሔር እንዲሰራ ከምትጥር እቅድህን በእርሱ ዙሪያ ስራ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ጊዜህን በጥበብ ተጠቀምበት ምክንያቱም አንዴ ካጠፋኸው በፍጹም ተመልሰህ ማግኘት አትችልም።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon