ኢየሱስም መልሶ፣”እውነት እልሀለሁ፤ማንም ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም” አለው፡፡ – ዮሐ 3፡3
ለሆነ ሰው ስለ እምነታችሁ ስትነግሩ ሀይማኖትን ነው የምትሰብኳቸው …ወይስ ግንኙነትን?
መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ዳግመኛ መወለድ አለብን (ዮሐ 3፡1-8ን ይመልከቱ)እንጂ ሀይማኖታዊ መሆን አለብን አይልም፡፡እንዳለመታደል ሆኖ ብዙ ጊዜ ሰዎች ወንጌልን ልክ እንደ የሀይማኖት ስርዐት ዝርዝር እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳለ ግንኙነት አድርገው አያቀርቡትም፡፡
ነገር ግን የክርስትና ደንቦችን መጠበቅ እና ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ክርስቲያን አያደርጋችሁም ልክ ጋራጅ ውስጥ መቀመጥ መኪና እንደማያደርጋችሁ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ ደንቦችና ስርዐቶች ጠንካራ፣ከባድ እና ጫናን የሚፈጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ኢየሱስ ግን ለሰዎች የሚፈልገው ያንን አይደለም፡፡ኢየሱስ የሚፈልገው ሰዎች ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ነው፡፡
አንድ ሰው “ሀይማኖታችሁ ምንድነው?” ብሎ ቢጠይቅ ስለምንካፈልበት ቤተ-ክርስቲያን ከማውራት ይልቅ ከኢየሱስ ጋር ስላለን የግል ግንኙነት ነው ማውራት ያለብን፡፡ያንን ጥያቄ መመለስ የምፈልገው “ስለጠየቃችሁኝ አመሰግናለሁ እኔ ምንም ሀይማኖት የለኝም ነገር ግን ኢየሱስ አለኝ፡፡”ብዬ ነው፡፡
ሰዎችን “ኢየሱስን ታውቁታላችሁ? ጓደኛችሁ ነው?ከእርሱ ጋር የግል ግንኙነት አላችሁ?” ብለን መጠየቅ መጀመር አለብን::
ከዚህ በኋላ አንድ ሰው ስለ እምነታችሁ ሲጠይቃችሁ ስለ ግንኙነት አውሩለት ስለ ሀይማኖት አታውሩ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ አንድ ሰው እውነተኛ ክርስቲያን ለመሆን ዝርዝር ደንቦችን መከተል አለበት ወደሚል ወጥመድ ውስጥ መግባት ቀላል ነው ነገር ግን አንተ ከእኔ የምትፈልገው እምነት እንደዚያ ያለ አይደለም፡፡ከአንተ ጋር ህይወታቸውን ወደሚቀይር ግንኙነት ሰዎችን የሚጋብዝ ወንጌል እንድናገር ሀይልህን ስጠኝ፡፡