“ጠንካራ ምግብ” የሆነውን የእግዚብሔርን ቃል መመገብ

ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ለበሰሉ ሰዎች ነው፡፡ – ዕብራ 5፡14

ልጆቼን እንዴት እመግባቸው እንደነበረ ሳስብ ኮክ እና ሙዝ እስካገኙ ድረስ ሁሉም ነገር ጥሩ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ልክ ግን ማንኪያ ሙሉ አተር ማጉረስ ስጀምር መትፋት ጀመሩ፡፡ከዛ አተሮቹን ልጬ እንደገና ማጉረስ ጀመርኩ፡፡ትንሽ ጊዜ ቢወስድብኝም ግን በፍጥነትም ይሁን በዝግታ አተር መብላት ጀመሩ፡፡

የልጅ ክርስቲያንም ነገር እንደዚያው ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ ስንጀምር መንፈሳዊ ዕድገት ማደግ እንጀምራለን፡፡በስጋ መመላለሳችንን አቁመን እሱ እንድናደርገው የሚፈልገውን ማድረግ እንፈልጋለን፡፡

ምሳሌ 4፡18 በእግዚአብሔር ቃል ስንቀጥል የጽድቅ መንገድ በየቀኑ እየበራ እና እየጠራ እንደሚሄድ ይነግረናል፡፡እዚህ ጋር ቁልፉ ቃል መቀጠል የሚለው ነው፡፡የእግዚአብሔርን ቃል እንዲለውጠን መውደዳችንን፣ማጥናታችንን፣መስማታችንን መቀጠል አለብን፡፡

በቢጫ መብራት ነድታችሁ ታውቃላችሁ? ምናልባት ቸኩላችሁ ማለፍ እችላለሁ ብላችሁ አስባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ይሄንን ደጋግማችሁ ማድረግ ከቀጠላችሁ ችግር ውስጥ መውደቃችሁ አይቀርም፡፡የእግዚአብሔርም ቃል ነገር እንደዚሁ ነው፡፡

ማድረግ እንደሌለብን የምናውቀውን ነገር አድርገን ለማምለጥ የምንሞክር ከሆነ መጎዳታችን ላይቀር ይችላል፡፡የእግዚአብሔር ቃል እዚህ ያለው ሊጠብቀን ነው፡፡

ዕብራ 5፡14 ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ለበሰሉ ሰዎች ነው፡፡ ይላል፡፡

ጠንካራው የቃሉ ምግብ ይወቅሳችኋል እናም ያ ጥሩ ነገር ነው፡፡መንፈስ ቅዱስ ነው በልባችሁ አመለካከታችሁ ልክ እንዳልሆነና በተሳሳተ መንገድ ላይ እንዳላችሁ እንድታውቁት የሚያደርገው፡፡

ህይወትን በትክክለኛው አቅጣጫ ለመኖር ቃሉ ቁልፍ ነገር ነው፡፡ስለዚህ ህጻናት አትሁኑ…የቃሉን ጠጣር ምግም ተመገቡ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ለማደግ ቃልህ ብቸኛው መንገድ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡በክርስቶስ እንድሆን የፈጠርከኝን አይነት ሰው እንድሆን ጠጣሩን የቃልህን ምግብ ስመገብ ምራኝ እንዳድግም እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon