ጥርጣሬያችሁን አሸንፉት

ጥርጣሬያችሁን አሸንፉት

በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን። – 2 ኛቆሮ፡ 10፡5

አዕምሯችንን ለማደስና ለመቀየር ስንነሳ የሚያጋጥሙን በርካታ ችግሮች ይኖራሉ፡፡ እግዚብሔር ፍፁም አለመሆናችንን ያውቃል ስለዚህም ሁልግዜ መስመራችንን እንዳንስት ከጎናችን አለ፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ ሰይጣንም እኛ ፍፁም አለመሆናችንን ያውቃል ፤ ይህንንም በእያንዳንዱ መንገዳችን ላይ እኛን ለማስታወስ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

መልካም ነገሮችን እያደረግን ፣ እግዚብሔርን እያገለገልን ፣ በእምነትም እየተራመድን ድንገት ግን ያለምንም ምክንያት ለአንድ ቀን ወይም ለአንድ ሳምንት ያህል የአእምሮ ጥቃት ይደርስብናል፡፡ ሰይጣን ለአዕምሯችን እንደወደቅን ፣ በቂ እንዳልሆንን ፣ እግዚያብሔር እንደማይወደን እየደጋገመ ይናገራል፡፡

ምስጋና ለእግዚያብሔር ይሁንና የእግዚብሔር ቃል በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ምን ማድረግ እንዳለብን ይናገራል፡፡ 2ኛቆሮ 10፡5 እያንዳንዱ ሃሰብ ለእግዚያብሔር እንድናስገዛ ይናገራል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ውሸት ሲነገራችሁ ወደ ቃሉ ሒዱና ተቃወሙት፡፡

ጥርጣሬዎች ወደ ህይወታችሁ ሲመጡ እና ተስፋ ሊያስቆርጧችሁ ሲሞክሩ ወደ እግዚያብሔር አቅርቧቸው፡፡ ሁልግዜም ይሰራል!


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ሰይጣን ወደ እኔ የሚያመጣውን ውሸትና የክፉ ምክሩን ከእኔ ማራቅ እሻለሁ ቃልህም የሚለውን ላምንና ሃሳብህንም ገንዘቤ ማድረግ እሻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon