
ትዕዛዝህን አሰላስላለሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ። – መዝ 119፡15
ጥልቅ ጉዳት ልክ ከሥራ ማጣት ወይም በስራ ውስጥ የምንፈልገዉን ዕድገት እንደማጣት ካሉ ከትላልቅ ቅሬታዎች ብቻ አይመጣም፡፡ ጥልቅ የስሜት ጉዳት ሊመጣ የሚችለዉ ተከታታይ ከሆኑ ጥቃቅን ንዴቶችና ብስጭቶች ነዉ፡፡ ለዚህ ነዉ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ጥቃቅን ቅሬታዎች አያያዝ ማወቅ ያለብን፡፡
አንድ ነገር ላይ በተከታታይነት የምታተኩር ከሆነ ማሰላሰል ይባላል፡፡ በየቀኑ የሚመጡ ትናንሽ ብስጭቶች በራሳቸዉ አናዳጅ ናቸዉ፤ ጭራሽ ሲጠራቀሙማ ሌላ ነገር ማሰላሰል የማይቻል ሁላ ይመስላል፡፡
በችግርህ ላይ ከማተኮርና በመበሳጨት ፈንታ በእግዚአብሔርና እርሱ ላንተ ባለዉ ተስፋ ላይ አተኩር፡፡ ህይወት ወደታች ልትጫንህ ትችል ይሆናል ነገር ግን እታች አትቆይ፡፡ እግዚአብሔር ከፍ ሊያደርግህ ዝግጁ፣ ብቁና ፈቃደኛ ነዉ፡፡
ቅሬታ ወደ ታች ሲጫንህ፣ ወይ ወደ ታች እንዲያሰምጥህ ልትፈቅድለት ትችላለህ ወይም ደግሞ እንደ መረማመጃ ድንጋይ ተጠቅመህ የተሻለ ነገር ለማየት መጠቀም ትችላለህ፡፡ ቅረታን እንደአመጣጡ ተቀብለህ በእግዚአብሔር መንገድ ለማሰለሰል ምረጥ፡፡ እርሱ ለአንተ የተሻለ ነገር አለዉ ቅሬታህን እንድታሸንፍም ይረዳሃል፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ልክ መዝሙር 119፡15 እንደሚለዉ ቃልህን አሰላስላለሁ ወደ ታች ሊያወርደኝ የሚመጣዉን ትንንሽ ቅሬታ እተዋለሁ፡፡ ቃልህ ሀይለኛና ህይወት ሰጪ ነዉ፡፡ ስለዚህ አንተን በማየት ቅሬታን ማሸነፍ እንደምችል አምናለሁ፡፡