እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። – ያዕ 5:16
እኔ ቀላል፣ ከልብ የሆነ እና በእምነት የተሞላ ጸሎት የእግዚአብሔርን ትኩረት እንደሚያገኝ ተምሬአአለሁ፡፡ ያለመታደል ሆኖ ዘወትር ይህንን አሳንሰን እናይና በትልልቅ ኩነቶች ላይ እናተኩራለን፡፡ ሐቁ ግን ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ መግባባት ነዉ፡፡
በምንጸልይበት ጊዜ ራሳችንን ለማስደነቅ እንዳንሞክር እንጠንቀቅ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንደበተ ርቱዕ እንደሆንን አስባለው፤ በድምጻችንና በቃሎቻችን እግዚአብሔርን ማስደነቅ እንፈልጋለን ነገር ግን እግዚአብሔር የሚፈልገዉ በቃ እንድናወራዉ ነዉ፡፡
እርሱ የሚፈልገዉ ልክ ለጓደኛችን እንደምናወራዉ እንድናወራዉ ነዉ ምንም የተለየ ድምጽ ሳንጠቀም፡፡ በቀን ዉሎአችን የማንጠቀመዉን አማርኛ በጸሎታችን መጠቀም አያስፈልገንም፡፡
ለሰዓታት ያለማቋረጥ መጸለይም ላይጠበቅብን ይችላል፤ ጸሎታችንን በጊዜ ገደብ በፕሮግራም ማድረግም ጥሩ ነዉ፡፡ እንከምንጨርስ ድረስ መጸለይ ከዚያም ወደ ስራችን መሄድ በድጋሚ መጸለይ ሲያስፈልገን ደግሞ መጀመር እንችላለን፡፡
ብቸኛዉ በጸሎት የምትረካበት መንገድ ጸሎትን እግዚአብሔርን ለማምለክና እርሱ ስላደረገልህ ነገር ለማመስገን እንደ እድል ስትጠቀመዉ ነዉ፡፡ እርዳታዉን ጠይቅ እርሱን በሁሉም ነገርህ ዉስጥ አስገባዉ፡፡ እዚህ ያለዉ ለማስደነቅ ሳይሆን ከአንተ ጋር ለመኖር ነዉ፡፡ ሥራ አታድርገዉ በቃ እርሱን ወደ ዉስጥ ጋብዘዉ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ጸሎትን እንደ ሥራ እንዳከነዉነዉ አትፍቀድልኝ፡ አንተን ለማስደነቅ በተወሰነ መንገድ ወይም ለተወሰነ ሰዓት መጸለይ አልፈልግም፡፡ አንተ የቅርብ ጓደኛዬና የሁሉም የህይወቴ አካል እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡