ጸጋን መረዳት፣በእምነት መራመድ

ጸጋን መረዳት፣በእምነት መራመድ

በእምነት፣በጸጋ ድናችኋልና፤ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፡፡ – ኤፌ 2፡8

ብዙዎቻችን የዳንነው በጸጋ እንደሆነ እናውቃለን ነገር ግን ምን ያህል ሰዎች በእውነት የእግዚአብሔርን ጸጋ ሀይል ያውቁ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

ሁሉም ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ነገር የሚመጣው በጸጋ በእምነት በኩል ነው፡፡ስለዚህ ጸጋን ስትረዱ በእምነት ተራምዳችሁ የእግዚአብሔርን በረከቶች ትቀበላላችሁ፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ የተወሳሰበ ወይም ግራ የሚያጋባ አይደለም፡፡ቀላል ነው ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ያልገባቸው። ከጸጋ የሚበልጥ ሀይለኛ ነገር የለም፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው ማንኛውም ነገር-ደህንነት፣የመንፈስ ቅዱስ ሙላት፣ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድግ እና በህይወታችን ያለ ማናቸውም ድል-የሚመሰረተው በእርሱ ላይ ነው፡፡ያለ ጸጋ ምንም ነን፣ምንም ማድረግ አንችልም፡፡

ዛሬ ስለጸጋ ብቻ አትስሙ፣ነገር ግን በህይወታችን ያለ ማናቸውም ነገር የሚደገፈው በችሎታዎቻችን፣በስራችን እና በእውቀታችን ላይ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር ገደብ የለሹን ሀይሉን ፍላጎቶቻችንን ለመሙላት ለመጠቀም መፍቀዱ ላይ ነው፡፡ይህ ጸጋ ነው፡፡

ዛሬ እዚህ እውነት ላይ አተኩሩና እምነታችሁ ሲያድግ ተመልከቱ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ እውነተኛውን ሀይሉን ሳልረዳ ስለጸጋህ መስማት ብቻ አልፈልግም፡፡ጸጋህ እንዴት አስደናቂ እንደሆነ እንድረዳ እና እምነቴ በአንተ እንዲያድግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon