ጻድቅ ቁጣ እና ኃጢዕት ምላሽ

ጻድቅ ቁጣ እና ኃጢዕት ምላሽ

ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። – ኤፌ 4፡26-27

ሁሉም ቁጣ ኃጢአት ነዉን? አይደለም! ነገር ግን አንዳንዱ ቁጣ ኃጢአት ነዉ፡፡ እግዚአብሔር እራሱ በኃጢአት ላይ ፣ በኢ-ፍትሃዊነት ላይ፣ በአመጽና አሰፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ የጽድቅ ቁጣ ይቆጣል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቁጣ ጠቃሚ ዓላማን ያገለግላል ስለዚህ ሁል ጊዜ ኃጢአት አይሆንም።

በግልጽ የሚጎዱ ስሜቶች ሊኖሩን ይችላሉ ባይሆን እግዚአብሔር ራስን የመግዛት ፍሬ ባልሰጠን ነበር፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ መፈተን ኃጢአት አይደለም ፤ ኃጢአት የሚሆነዉ ሳትቋቋመዉ ስትቀርና ስታደርገዉ ነዉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መቆጣት የግድ ስህተት ላይሆን ይችላል ነገር ግን ወደ ኃጢአት ተግባር ሊመራን ይችላል፡፡

እኛ አግባብ ባልሆነ መንገድ እንደ ተያዝን እንድንገነዘብ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ቁጣን እንድናስብ ይፈቅድልናል፡፡ ነገር ግን በህይወታችን ገሃድ ኢ-ፍትሃዊነት ቢፈጸምም ቁጣችንን ግን አለአግባብ መጠቀም የለብንም፡፡ ቁጣ ወደ ኃጢአት እንዳይመራን መከላከል ይጠበቅብናል፡፡

ኤፌ 4፡26 የሚነግረን ስንቆጣ ኃጢአት እንዳናደርግ ነዉ፡፡ የግድ ቁጣህ ኃጢአተኛ መሆን የለበትም ግን ደግሞ ኃጢአታዊ መልስ እንድትሰጥ እንዳይመራህ ቁጣህን ለጌታ መስጠትህን እርግጠኛ ሁን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ቁጣን ከኃጢአት በጸዳ መንገድ እንድጠቀም እርዳኝ፡፡ ቁጣዬን እንድትቆጣጠረዉ ለአንተ እሰጣለሁ ፤ ነገሮችን ሁሉ ለበጎ እንደምታደርግልኝም አምንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon