ፀልይና ታዘዝ

ፀልይና ታዘዝ

አቤቱ አንተን የምሰማበትንና የምታዘዝበትን አቅም ሰጠኸኝ፡ መዝ. 40÷6

ለብዙ ዓመታት እግዚአብሔር እንድናገኝ እፈልግ ነበር፣ ነገር ግን እርሱን የምታዘዛቸውን ነገሮች ግን ከውስጥ እመርጥ ነበር፡፡ እንዲሁም እርሱ አድርግ ከሚለኝ ውስጥ ቀላሉንና እንደ እኔ ሃሣብ መልካም የመሰልኝን ሃሣብ ብቻ አደርጋለሁ፡፡ የሰማሁት ነገር ደስ ካላለኝ ደግሞ ነገሩ ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ በመቀጠር እተዋለሁ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ እግዚአብሔር ለአንተ የምልህ ነገር የሚመስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የማይመቹ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን አንተ ዝም ብለህ በእምነት ብትታዘዝ ለመልካም አይሆንልህም ማለት አይደለም፡፡ ለምሣሌ እግዚአብሔር ለማትወደውና ለማትግባባው ሰው እንዳትታዘዝ ብነግርህና አንተም መልሰህ ይቅርታ ጠይቀህ ብትፀልይ እንኳ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ድምፅ በጉዳዩ ላይ ብትሰማ እንኳ ለእግዚብሔር አልታዘዝክም፡፡

ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞዬ እንዲሁም አገልግሎቴ ወደኋላ ዞር ብዬ ስመለከተው ቀላል የሆነ ማብራሪያ ለአገልግሎታችን ስኬትና ደስታ ለእኔና ለባለቤቴ ዳዊት የተማርከው ነገር መፀለይ፣ ከእግዚአብሔር መስማትና እርሱ አድርጉ ያለንን ማድረጋችን ነው፡፡ ለዓመታት በሕይወቴም እንደተለማመድኩት በሥራዬ ተሳካልኝ የምለው ነገር ቢኖር በቀላሉ መፀለይና መታዘዝን ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ነገር የአደባባይ ባይሆንም ለእኔ ውጤታማ ሥራ ሆኖልኛል፡፡

የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሕይወትህ ከፈለክ በእርግጠኝነት የምልህ ነገር በመፀለይ ታዘዝ እግዚአብሔርም ለሁለቱም ብቃትን ይሰጥሃል፡፡ ይህንንም በማድረግ ብትቀጥል በሕይወትህ ዘመን ወደ ፊት በስኬት ትጓዛለህ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃለ ለአንተ፡- ፀልይ፣ ከልብህ ሥማ፣ የሰማየሁን ታዘዝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon