ፈገግ በል/ ተደሰት!

ፈገግ በል/ ተደሰት!

ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፤ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች። – ምሳ 15፡13

ሰው ሁሉ ፈገግ ማለትን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር ከሰጠን ስጦታዎች መካከል ፈገግ ማለት አንዱ ነው፡፡ ፈገግታ ሌሎች ሰዎች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ሰዎች የሚያምሩ ሆነው የሚታዩት ፈገግ ሲሉ ነው፡፡ በህይወትህ ውስጥ ያለው ደስታ ግልፅ ሲሆን ወደ ሌሎች ሰዎች ይተላለፋል። ነገር ግን በውስጥህ ያለውን የእግዚአብሔርን ደስታ ቆልፈህበትና በፊትህ እንዲታይ ሳትፈቅድለት ስትቀር በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ደስ የሚል ልምምድ እንዳይኖራቸው እየከለከልካቸው ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ደስታን መግለጽ ያሉበትን ሁኔታና ምናልባትም የሌሎችን ሁኔታ ሊቀይር እንደሚችል አይረዱም፡፡ ሕይወትን በጌታ ተደስቶ መኖር የሚያስጨንቁ መጥፎ ሁኔታዎችን ለማሸነፍ ይረዳል፡፡ በውስጣዊ ማንነታችን የእርሱ ደስታ ሲኖረን በውጫዊ ፈገግታችን ከመግለጽ ውጪ ምርጫ የለንም፡፡

ፈገግታ ይህንን ያህል ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ትንሽ ፈገግታ ምን ያህል ሕይወትን ሊቀይር እንደምትችል እግዚአብሔር አሳይቶኛል፡፡ በፈገግታ የተረጋጋ ደስታን መግለጥ መልካም ነገሮችን ወደ ህይወታችሁ ያመጣል፣ የጌታን ደስታና ብርሃን  ለሌሎች እናካፍላለን፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ በየዕለቱ ፈገግ እንድል አሳስበኝ፡፡ ታላቅ ደስታን ሰጥተኸኛል፡፡ ይህንን ደስታ ማሳየትና የሌሎችን ሕይወት ብሩህ ማድረግ እፈልጋለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon