
‹‹ … አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም›› (መዝ.38፡9) ።
እግዚአብሔር በቃሉ እንደተናገረው እኛ በእርሱ ደስ ሲለን፤ እርሱ የፍላጎታችንን ምስጢርና የልባችንን ልመና ይሰጠናል (መዝ. 37፡4)፡፡ ይህንን እቅድ እወደዋለሁ ምክንያቱም እኔ በእርግጠኝነት ለብዙ ዓመታት አንድ ነገር ለራሱ ለማግኘት ስጥር ብዙ ተስፋ መቁረጥ ደርሶብኛል፡፡ አንዳንድ ነገሮችን በመፈለግ ሂደት ውስጥ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔርን አጥብቀን ስንፈልግ እንከስራለን፤ እርሱን ማወቅን ስናገኝ ግን ደስተኞች እንሆናለን፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት እኔ ለአገልግሎቴ ከነበረኝ ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ በራሴ እንዲህ ዓይነት ነገሮች አጋጥሞኛል፡፡ በዓለም ላይ እጅግ በጣም ወሳኝ አስፈላጊ ነገር ነው ብዬ አስብ ነበር፡፡ ነገር ግን በኋላ የተረዳሁት በጣም ወሳኝ ነገር ቢኖር እግዚአብሔርን ማገልግል ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
ፍላጎቶችህን በሚዛናዊነት እየያዝክ ነውን? እንዲሁም ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በላይ በእግዚአብሔር ደስተኛ ነህን? አይደለም የምትል ከሆነ መለስ ብለህ በእውነት የትኛው ነገር በጣም ወሳኝ አስፈላጊ ነገር እንደሆነ በማገናዘብ ራስህን መልሰህ መገምገም አለብህ፡፡ የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚያስተምረን ሁሉንም ፍላጎቶቻችንን በእግዚአብሔር ፊት አኑራቸውና ከእርሱ ፍጹም ፈቃድ ጋር የማይስማማውን ማንኛውንም ነገር ለማስወገድ በእርሱ ታመን፡፡
ሁሉም ፍላጎቶቻችን ከእግዚአብሔር አይደሉም ስለዚህ እኛ ያለንን ሁሉንም ፍላጎቶች ጋር መገናኘት የለብንም፡፡ ነገር ግን ለእኛ መልካም እንዲሆን ከሚያስፈገው ፍላጎቶች ጋር እንድንገናኝ እግዚአብሔርን መታመን እንችላለን፡፡ አንድ ነገር ለምነህ ያንን የለመንከውን ነገር ባታገኝ ምናልባት እርሱ አንድ የተሻለ ነገር ለአንተ እንዳለው በአዕምሮህ እንድታውቅ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተረጋጋ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ እርሱ የቀረውን የህይወትህ ነገር ሁሉ ያስባል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር እቅድ የራስህ ከሆነው እቅድ የበለጠ ነው፡፡