ፍቅርህን ፈትን (መዝን)

« … እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ፥ እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?»(ዮሐ.13፡12)።

በህይወታቸው የተጠበቁና ደህንነትየሚሰማቸው ሰዎች ብቻ እውነተኛ አገልጋይ ሊሆኑ አንደሚችሉ አምናለሁ። ኢየሱስ መጎናጸፊያውን ደርቦ የደቀመዛሙርቱን እግር ለማጠብ ችሎ ነበር፣ ምክንያቱም እርሱ ማን እንደሆነ፣ ከየት እንደመጣ፣ ወደየት ሊሄድ እንዳለ ያውቅ ነበር። እርሱ ምንም ፍርሃት አልነበረውምና ምንም መፈተን አላስፈልገውም፣ ስለዚህ እርሱ ለማገልገል ነጻ ነበር።

በማህበረሰባችን ውስጥ ብዙ ሰዎች ተቀባይነትንና ዋጋ ያላቸው መሆናቸው እንዲሰማቸው ለማድረግ ከፍተኛውን ሥፍራ ይፈልጋሉ።ብዙውን ጊዜ አገልጋይ የሚታየው እንደ የበታች ሥራ ነው፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር አዕምሮ ይህ ትልቁ የደረጃ ሥፍራ ነው። እውነተኛ አገልጋይ መሆን የሚጀምረው ከትሁት ልብ ነውና ይህ የትሁት ልብና መንፈስ ማለት በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያገኘ ማለት ነው። ስለተፈጥሮአዊ ችሎታችን ምንም አይደለም፣ የእኛ ከእግዚአብሔር የጠላከው ጥሪያችን ግን እርሱንና ሌሎችንም ማገልገል ነው።

የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠብ ውስጥ ኢየሱስ እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ምሳሌን ሰጣቸውና ሌሎችንም የሚያገለግሉ ከሆነ እንዲህ እንዲያድርጉ ተናገራቸው፤ እነርሱም በዚህ ደረጃ የሚጥሩ ከሆነ የተባረኩና ደስተኛ ይሆናሉ (ዮሐ.13፡17 ተመልከት)። እኛ እርስ በርሳችን የምናገለግል ከሆነ፣ እኛ አንዳችን የሌላችን አካል ክፍል እንሆናለን። ትክክለኛውን ትርጉም ያለውን ፍቅር እንለማመዳለን። ኢየሱስ ከሁሉም የበለጠ የበላይ ነው፣ ነገር ግን እርሱ በራሱ ትህትና አገልጋይ ሆነ። አሁን የእርሱን ፈለግ ለመከተል ፈቃደኛ ነህን?


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ብዙ ሰዎችን መርዳት የምትችለውን ያህል እርዳ፣ ሁልጊዜ እስከምትችለው ድረስ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon