ፍጹም ልብ

ፍጹም ልብ

እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ስንፍና አድርገሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። – 2 ዜና 16፡9

ከጊዜ ወደ ጊዜ እግዚአብሔር በህይወቴ ያስታወሰኝ ነገር እርሱ ከእኛ የሚፈልገዉ ፍጹም ብቃት ሳይሆን ፍጹም ልብ እንደሆነ ነዉ፡፡

ብዙ ሰዎች እያንዳንዱ የህይወታቸዉ ክፍል ፍጹም እስኪሆን ድረስ እግዚአብሔር እነርሱን የማይጠቀማቸዉ ይመስላቸዋል፡፡ እንደዚያ ዓይነት አመለካከት ሰዎች እግዚአብሔር በሕይወታቸዉ እንዲሰራ ከመፍቀድ ይከለክላቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እኛን ስለእኛ ሳይሆን ከእኛ ባለፈ ይጠቀመናል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በብቃትህ ተመስርተዉ “ይወዱሃል”፡፡  እንድትሰራ የሚፈልጉትን ነገር ስታደርግ ይቀበሉሃል እሱን ካላደረግህ ደግሞ ይቃወሙሃል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር የተመሰረተዉ በራሱ ላይ ነዉ፡፡ የሚወድህም የሚቀበልህም እንዳለህ ነዉ፡፡

ይህ ማለት ግን የወደቀ አስተሳሰብ እንዲኖረንና የቅድስናን ህይወት አንፈልግ ማለት አይደለም፡፡ ልቡ ንጹህ የሆነ ሰዉ እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚናፍቅና የሚና ነዉ ፤ ስለድካሙና ስለ ስህተቱ እግዚአብሔር እንደማይቀበለዉ አያስብም፡፡ እርሱ ሊወደንና በድካማችን ሊያግዘን ነዉ የሚፈልገዉ፡፡

እግዚአብሔር ይዉደድህ አንተም በምላሹ ንጹህ ልብ ስጠዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከድካሜና ከእንከኔ ባሻገር እንደምትወደኝ አዉቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፍቅርህ አመሰግናለሁ እንደምትሰራብኝም አዉቄ በንጹህ ልቤ እከተልሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon