ሁለመናችሁን ለእግዚአብሔር መስጠት

ሁለመናችሁን ለእግዚአብሔር መስጠት

እግዚአብሔርን በሀብትህ፣ከምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፤ይህን ብታደርግ፣ጎተራህ ሞልቶ ይትረፈረፋል፤መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ ይሞላል፡፡ – ምሳ 3፡9-10

ብዙ ሰዎች ከእግዚአብሔር መቀበል ይፈልጋሉ፡፡ነገር ግን ሁለመናቸውን ለእርሱ መስጠት አይፈልጉም፡፡እውነታው ለሁላችንም ህይወታችንንና የልባችንን ሁኔታ በተደጋጋሚ መገምገም በእግዚአብሔር ላይ አተኩረን እንድንቀጥልና ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነን በልባችን ያስቀመጠውን ሁሉ እንድናደርግ ይረዳናል፡፡ እናም አንዳንዴ እንዳዲስ ሰጪዎች ለመሆን፣ጊዜያችንን ፣እራሳችንን  እና ገንዘባችንን ለጌታ ስራ ለማዋል ኪዳን ማደስ አለብን፡፡

በሚያስፈሩ ሀሳቦች በኩል ሰይጣን ከመስጠት እንዲያስቆማችሁ አትፍቀዱለት፡፡ኢየሱስ ስለምንም ነገር እንዳንጨነቅ ነግሮናል፡፡እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ያውቃል እናም እንደሚጠነቀቅልን የተስፋ ቃሉን ሰጥቶናል (ማቴ.6፡25-34)፡፡

ምሳሌ 3፡9-10 ሲናገር እግዚአብሔርን በሀብትህ፣ከምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፤ይህን ብታደርግ፣ጎተራህ ሞልቶ ይትረፈረፋል፤መጥመቂያህም በአዲስ የወይን ጠጅ ቲፍ ብሎ ይሞላል፡፡ያላችሁን ሁሉ ለእግዚአብሔር ስትሰጡት እናንተን ለመጠበቅ ታማኝ ይሆናል፡፡

ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ፡፡የሆናችሁትን ሁሉ፣ልትሆኑ ተስፋ የምታደርጉትን፣ህልሞቻችሁን፣ራዕዮቻችሁን፣ተስፋዎቻችሁን እና ፍላጎታችሁን  ለእርሱ ስጡት፣  ሁሉንም ነገር የእርሱ አድርጉት፣እናም እርሱ ሀይሉን በህይወታችሁ በኩል ይገልጻል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ዛሬ ሁለመናዬን ፡እጆቼን፣አንደበቴን፣አዕምሮዬን፣አካሌን፣ገንዘቤን እና ጊዜዬን እሰጥሀለሁ፡፡ያለኝ ማናኛውም ነገር የአንተ ነው፡፡ዛሬ ፈቃድህን መፈጸም እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon