«… ጸልዩልን፤ በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፥ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና»(ዕብ.13፡18)።
እግዚአብሔር ከመከራ ወይም ከፈተና ህይወት እንድንወጣ ህሊናን ይሰጣል። እና ህሊናችን የሚናገረውን ቸል ካልን ኃጢአትን ስናደርግ የሚመጣብንን የህሊና ነቀፌታ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ወቀሳ የሚሰማን የነቃን ለመሆን አንችልም። ሰዎች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መልካምና ክፉን የሚለዩበት የሚሰማቸውን ነገር ቸል ለማለት ልባቸው ይደነድናል። ይህ ዓይነት ጉዳይ ዳግም የተወለዱትን ጭምር ላይ ይታያል። ሰዎች ልባቸው እየደነደነ በሄደ ቁጥር የእግዚአብሔርን ድምጽለመስማት የበለጠ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። ህሊናቸውም እግዚአብሔር እንዲሰራ አስቀድሞ ባበጀው ልክ የማይሠራ ይሆናል።
ህሊና የመንፈስ ሥራ ስለሆነ የሚሠራውም ባህሪያችን ልክ እንደ ውስጥ ተቆጣጣሪ በውስጣችን ይሠራል። አንድ ነገር መልካም ወይም ክፉ ከሆነ በውስጣችን እንድናውቅ ያደርጋል፣ በውጤቱም የአንድን ነገር ደረጃ ውም መስፈርት ወይም መመሪያ እውቀታችን እግዚአብሔር እንዳስቀመጠው ሲሆን በህሊናችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የሚፈጠር ይሆናል።
የእርሱ ቃል ህሊናችን ከተኛበት የስልምታ ዓይነት እንዲነቃ ያደርጋል። በዳግም ልደት ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች አንድን የተሳሳተ ነገር ካደረጉ በኋላ ይሆናል ስህተቱን የሚያውቁት፣ ነገር ግን ዳግም ተወልደው ጌታን እንደተቀበሉ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ አልተሞሉም እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር በመደበኛነት በየቀኑ ህብረት ስለማያደርጉ ነውየወቀሳ ስሜት እይሰማቸውም።
በኦግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ብዙ ባሳለፍን ቁጥር፣ የእግዚአብሔርን ልብ ለማይገልጥ ነገር ይብልጥ የነቃን የሚሰማን እንሆናለን። ዓለማዊበሆነ መንገድ ስንራመድ ኢየሱስ ሁኔታዎችን እንድንቆጣጠር ከሚፈልገው መንገድ በመውጣችን እኛ ፈጥንን በውስጣችን ይሰማናል። አዕምሮአችንን በእግዚአብሔር ቃል ስንሞላና ከዚያም ህሊናችንን በቀላሉ ስንታዘዝ የሚያስደንቅ ህይወት መኖር እንችላለን።
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ህሊናህ ያንተ መመሪያ እንዲሆን ፍቀድለት።