ህይወት እንዳቀድነው ሳይሆን

ህይወት እንዳቀድነው ሳይሆን

እግዚአብሔር፣ለሚወዱትና እንደ (እርሱ) ሐሳቡ ለተጠሩት፣ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ (በእቅዱ መሰረት) እንደሚያደርግላቸው (እግዚአብሔር የልፋታቸው ተካፋይ ሆኖ) እናውቃለን ፡፡ – ሮሜ 8፡28

ሐዋሪያው ጳውሎስ በሮሜ 8፡28 ላይ ነገሮች ሁሉ ተያይዘው ለበጎ እንደሚሰሩ ይነግረናል፡፡ጳውሎስ ነገሮች ሁሉ በጎ ናቸው እንዳላለ አስተውሉ ይልቁንስ ተያይዘው ለበጎ ይሰራሉ ነው ያለው፡፡

ጳውሎስ በተጨማሪ በሮሜ 12፡16 ላይ ተስማምታችሁ ኑሩ (ከሰዎች፣ከነገሮች ጋር) ይላል፡፡ሀሳቡ ነገሮችን የምናቅድ ነገር ግን እቅዱ ካልሰራ የማንሰባበር ሰዎች ስለመሆን ነው፡፡

ለምሳሌ መኪናችሁ ውስጥ ገብታችሁ ሞተሩ አልነሳ አላችሁ እንበል፡፡ሁኔታውን ልታዩ የምትችሉበት ሁለት መንገዶች አሉ፡፡ሁሌም የማቅደው አይሆንልኝም! ድሮም አውቀዋለሁ ማለት ትችላላችሁ፡፡ወይም እንግዲህ አሁን ከቤት መውጣት አልችልም ማለት ነው ግን ምንም አይደል ይሄ የእቅድ ለውጥ ለመልካም እንደሚሆንልኝ አምናለሁ፡፡እግዚአብሔር ሁሉንም ይቆጣጠረዋልማለት ትችላላችሁ፡፡

እግዚአብሔር ጭንቅላታችሁን ቀና የሚያደርገውና ክብራችሁ እንዲሆን ፍቀዱለት(መዝ 3፡3ን ይመልከቱ)፡፡ሁሉንም ነገር፡ተስፋችሁን፣አመለካከታችሁን፣ስሜታችሁን፣ጭንቅላታችሁን፣እጃችሁን፣ልባችሁን-መላ ህይወታችሁን ከፍ ሊያደርገው ይፈልጋል፡፡ህይወት እንደእቅዳችን እንኳ ባይሄድ እርሱ መልካም ነው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን በቁጥጥርህ ስር አድርገህ በስራ ላይ እንዳህ ስለማውቅ ህይወት ባቀድኩት መሰረት ሳይሄድ ሲቀር ቀለል አድርጌ አየዋለሁ፡፡እቅዶቼ ሳይሰሩ ሲቀሩ መልካም ነገር እንዳይ እና አዎንታዊ ሆኜ እንድቀጥል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon