ለክብር የሚሆን ዕቃ ናችሁ?

ለክብር የሚሆን ዕቃ ናችሁ?

እንግዲህ ማንም እራሱን ከእነዚህ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ቢያነጻ ለክቡር አገልግሎት የሚውል፣የተቀደሰ፣ለጌታው የሚጠቅም፣ለመልካም ሥራም ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ ይሆናል፡፡ – 2 ኛ ጢሞ 2፡21

መጽሀፍ ቅዱስ ስለ እኛ ሲናገር ሸክላ፣ደካማ ሰው የሆነ መገልገያ ዕቃ (2ኛ ቆሮ.4፡7ን ተመልከቱ) ይለናል፡፡በሸክላ ሰሪው እጅ እንዳለው ሸክላ እኛም የተሰራነው ከሸክላ ነው (ኢሳ.64፡8ን ይመልከቱ)፡፡ እንደ ዘፍ.2፡7 ሲናገር እግዚአብሔር አዳምን ከምድር አፈር ነው ያበጀው መዝ.103፡14ም እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል፡፡

ምንም እንኳ ደካማ እና ፍጹም ያልሆንን ሰዎች ብንሆንም ራሳችንን በቃሉ ስንሞላ ለእርሱ መገልገያነት ልንቀዳ የተዘጋጀን የበረከቱ መያዣ ዕቃዎች እንሆናለን፡፡ሁላችንም ለጌታ ጠቃሚዎች ነን-ጌታ የተሰነጠቀም ሸክላ ይጠቀማል!

መጀመሪያ ግን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር መንጻት አለብን፡፡2ኛ ጢሞ.2፡21 እንግዲህ ማንም እራሱን ከእነዚህ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ቢያነጻ (ንጹህ ካልሆነው፣ከሚያሳድፍ ነገር እና ከተበላሸ ነገር) ለክቡር አገልግሎት የሚውል፣የተቀደሰ፣ለጌታው የሚጠቅም፣ለመልካም ሥራም ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ ይሆናል ሲል ያስታውሰናል፡፡

ዛሬ የተለያቸችሁ ዕቃዎች ስትሆኑ እግዚአብሔር ለማመን የሚከብዱ  ነገሮችን በህይወታችሁ ይሰራል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ያንተ ነኝ፡፡ለአንተ አገልግሎት የሚጠቅም ዕቃ መሆን እፈልጋለሁ፡፡እራሴን ለአንተ እሰጣለሁ፡፡በቃልህ ተሞልቼ ለእኔ ላሰብከው መልካም ስራ ብቁ እና ዝግጁ መሆን እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon