ልዕለ ተፈጥሯዊ ሞገስ

ልዕለ ተፈጥሯዊ ሞገስ

እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል። – 1 ሳሙ 2፡7

ፍጥረታዊ በሆነ ሞገስ እና ልዕለ ተፈጥሯዊ በሆነ ሞገስ መካከል የሰፋ ልዩነት አለ፡፡ ፍጥረታዊው ሞገስ በጥረት ነው ፤ ልዕለ ተፈጥሯዊ ሞገስ ግን የጸጋ ስጦታ ነው፡፡

የመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሀፍ 2፡7 እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል ይላል፡፡ ይህንን ገላጭ ምሳሌ የሚሆነን የአስቴር ሕይወት ነው፡፡ እግዚአብሔር ከነበረችበት የዝቅታ ሕይወት በምድር ሁሉ ላይ ንግስት እንደትሆን አደረጋት፡፡ እግዚአብሔር ንጉስን ጨምሮ ባያት ሁሉ ፊት ሞገሱን አደረገባት፡፡

አስቴር ይህን ሞገስ ተጠቅማ ክፉ በነበው ሀማ ሊገደል የነበረው ሕዝብ እና ራሷን አስመለጠች፡፡ ምናልባት ወደ ንጉስ ገብታ ይህን ችግር ለመናገር እና ንጉስም ጣልቃ እንዲገባ ለማድረግ ትፈራ ይሁን እንጂ አሴቴር ከእግዚአብሔር የተሰጣት ሞገስ እንዳላት ታውቅ ነበር በፍጹምም ልበ ሙሉነት ማድረግ የነበረባትን አደረገች፡፡

እንደ አስቴር እኛም ከእግዚብሔር በተሰጠን ሞገስ ውስጥ በመኖር በፍጹም ነጻነት እና መፈታት ልንኖር ይገባናል፡፡ በሕይወታችን ከሚከሰቱ ሁኔታዎች በላይ ልዕለ ተፈጥሯዊ የሆነውን ሞገስ የሚያጎናጽፈውን ሞገስ እግዚአብሔርን እንመነው፡፡ ተስፋ ያጣንበት ጉዳይ እንኳን ቢሆን ከዚያ ውስጥ እግዚአብሔር ያነሳናል፡፡ ሕይወትህ በእርሱ እጅ ከሆነ የጌታም ብርሃን ያበራብሃል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ በፍጥረታዊ ሞገስ ላይ መደገፍ አልፈልግም ፡፡ በአንተ በሆነው ልዕለ ተፈጥሯዊው ሞገስ ውስጥ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ ይህን አውቃለሁ ሕይወቴ በአንተ እጅ ውስጥ ከሆነ አንተ ታነሳዋለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon