ሕዝብ የእግዚአብሔር ነው

ሕዝብ የእግዚአብሔር ነው

ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፣ በሥምህ ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ ኢሣ 43÷1

በጣም የሚጠቅምህ የእራስ ሃብት አለህ፣ የምታደንቀውና የምታንከባክበው አንድ ነገር አለህ; የሆነ ሰው በግድየለሽነት በአካባቢው የሆነ ነገር ቢወረውር ወይም የሆነ አደጋ ወይም ጥፋት የሚያስከትል ቢያደርግበት አታዝንም;

እግዚአብሔርም ተመሳሳይ የሆነ ስሜት ስለ እኛ ስለ ርስቱ ይሰማዋል፡፡ ሕዝብ የእግዚአብሔር ርስት ነው፡፡ እነርሱ ፍጥረቱ ናቸው፡፡ እናም በእርሱ ላይ ያለአግባብ ያልሆነ ነገር ሲፈፀም መንፈስ ቅዱስ ያዝናል፡፡ ማንም ሰው ተመሳሳይ የሆነ ጥሪ አይካፈልም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ደግሞ የተወለደ ግለሰብ ግን የእግዚአብሔር ወራሽና ከክርስቶስ ጋር አብሮ የሚወርስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የሠላም የጽድቅና የመደሰት መብት አለው፡፡ የፈለጉትን የማግኘት፣ ከእግዚአብሔር የመጠቀምና የእግዚአብሔር ቅባት በእነርሱ በኩል የማለፍ ሥልጣን አላቸው፡፡ እያንዳንዱ የአገልግሎቱን ፍሬ እኩል የማየት ዕድል አለው፡፡ ነገር ግን የእነርሱ ሌሎችንን የመውደድ ፈቃደኝነት በፍሬአቸው ላይ ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡ ከአመታት በፊት መንፈስ ቅዱስ ሲናገረኝ ‹‹አንደኛውና ዋነኛው ሰዎች በፍቅር የማይመለሱበት ምክንያት ትጋትን ስለሚጠይቅና በማንኛውም ጊዜ በፍቅር የምጓዝ ከሆነ አንድ የሆነ ነገር ዋጋ ያስከፍላቸዋል›› አለኝ፡፡ ፍቅር የሆነ ነገር ከምለው ጋር መስማማትን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ማድረግ የማንፈልገውን ነገርን ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ፍቅር መስጠት የማንፈልገውን ነገር ግን ልናኖር የምንፈልገውን መስጠትን ይጠይቃል፡፡ ፍቅር ለሰዎች ትዕግሥተኞች መሆንን ይጠይቃል፡፡ ሕብረቶች ሁልጊዜ ቀላል አይደሉም፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ ለሰዎች ጋር(ክብር) አለው፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን አንድን ውድ ዋጋ ያለውን ስለምፈልግ ዋጋ ከፍለንና ታግለን ሰዎችን መውደድ አለብን፡፡ እንጅ እርሱን ማሳዘን አይገባንም፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡- እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ የራሱ ሃብት ያያል፡፡ ስለዚህ ሰዎችን እንዴት እንደምትቀበል ወይም እንደምታስተናግድ ተጠንቀቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon