«ማርታ ማርታ»

«ማርታ ማርታ»

« …ኢየሱስም መልሶ፦ ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፥የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት» (ሉቃስ 10፡41 – 42)

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ታሪክ እንደሚመራን ኢየሱስ ሁለት እህትማማቾችን ለመጎብኘት ሄደ፡ ማርታና ማሪያምን። ማርታ ለእርሱ የማስፈልገውን ሁሉንም ነገር ለማዘጋጀት ማለትም ቤቱን ማጽዳት፣ ምግብ ማዘጋጀትና ሁሉንም ነገር በትክክለናው መንገድ ሠርታ ከእርሱ የሚገጥማትን አድናቆት ለማግኘት ትጥር ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ማሪያም ከኢየሱስ ጋር ህብረት ለማድረግ ያገኘችው አጋጣሚ ትጠቀም ነበር። ማርታ በእህቷ በጣም ተናደደችባት፣ ተነስታ መጥታ በሥራ እንድትረዳት አስጠነቀቀቻት። እርሷ በኢየሱስ ላይም ጭምር ቅሬታዋን በመግለጥ ለማሪያም እንደእርሷ በሥራ እንድትባዝን እንዲነግራት ነገረችው።

የኢየሱስ ምላሽ ግን «ማርታ፣ ማርታ» በማለት ጀመረ። እነዚህ ሁለት ቃላት ከመጀመሪያው በላይ የበለጠ እውነታውን የሚያረጋግጡ ናቸው። እነዚህ ቃላት የሚነግሩን ማርታ ከህብረት በጣም የባዘነች መሆኑን፣ እርሷ ከግንኙነት ይልቅ በሥራ መጠመድን እንደመረጠችና ጊዜዋን አለአግባብ እየጠቀመች እንዳለና ወሳኙን ነገር እያጣች እንዳለ የሚነግረን ነው። ማሪያም ግን በጥበብ የምትሠራ፣ የጊዜውን ጠቃሚነት የተገነዘበች ነበረች። እርሷ የቀረውን ጊዜዋን ሕይወቷን ለማንጻት ማሳለፍ ትችላለች፣ ነገር ግን በዚያን ቀን ኢየሱስ ወደ ቤቷ መጥቷልና እርሷ ለእርሱ እንኳን በደህና መጣህና ፍቅር ማሳየት ሰማት ነበር። እርሱ እርሷንና ማርታን ለማየት መጥቷል እንጂ የቤታቸውን ንጽህና ለመቆጣጠር አይደለም የመጣው። ንጹህ ቤት አስፈላጊ እንደሆነ አስባለሁ፣ አሁን ግን ለእርሱ ትኩረት የሚሰጥበት ጊዜ አልነበረም። የአሁኑ ጊዜ ለኢየሱስ ትኩረት የሚሰጥበት ነው ምክንያቱም እርሱ በዚያ አለና።

እኔ ራሴንም የማስታውሰውና አንተን የማበረታታህ ጥበብን እንድንጠቀምና የእግዚአብሔርን ህልውና በምናገኝበት ጊዜ እንዳያመልጥህ መጠንቀቅ አለብህ። መንፈስ ቅዱስ ለጸሎትና በእርሱ ህልውና ውስጥ ጊዜ አንድናሳልፍ ስሜታችንን የሚያነሳሳበት ጊዜ አለ፣ ነገር ግን እኛ ለሥራና ለጨዋታ ብለን ያን ጊዜ እናሳልፈዋለን። እርሱ ሲጠራን እኛ ወዳውኑ ምላሽ መስጠት አለብን። የህልውናው በረከት የበዛ፣ እኛ ማድረግ ከምንችለው ማናቸውም ነገር በላይ እጅግ በዛ ነውና።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ የምታገኘውን የደስታ አጋጣሚ ቸል አትብል

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon