ምላሳችሁን መቆጣጠር

ምላሳችሁን መቆጣጠር

አንደበትህነ ከክፉ ነገር ከልክል፤ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ፡፡ – መዝ 34፡13

እግዚአብሔርን ለማክበር ጠቃሚው ቁልፍ ምላሳችሁን መቆጣጠር ነው፡፡መዝ.50፡23 ሲናገር የምስጋናን መስዋዕት የሚሰዋ ያከብረኛል…ይላል፡፡

ከአንደበታችሁ የሚወጡት ቃላት እግዚአብሔራዊ ብቻ እንዲሆኑ በእያንዳንዱ ቀን አንደበታችሁን ለእግዚአብሔር ብትሰጡት ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?እያወራሁ ያለሁት የግላቹ ጊዜ ስትወስዱ ስለምታወጧቸው የምስጋና እና የአድናቆት ቃላት፣አዎንታዊ በሆነ መንገድ ስለመናገር ወይም እራሳችሁን ስለምታበረታቱበት ቃላት ብቻ አይደለም፡፡ የግንኙነቶቻችሁ ጤና የሚወሰነው በምትናገሩበት መንገድ እና ስለሌሎች በምታወሩበት  ነው፡፡

መዝሙር 34፡13 ሲናገር አንደበትህነ ከክፉ ነገር ከልክል፤ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ፡፡ይላል፡፡ለሌሎች ትዋሻላችሁ?ትሰድቧቸዋላችሁ?ወይም ስለ እነርሱ መጥፎ ነገርን ትናገራላችሁ?ወይስ ለምታገኙት ሰው ሁሉ ህይወት የሚሰጥ እና የሚያበረታታ ወደ ህይወታቸው ደስታን የሚያመጣ ቃላትን ትናገራላችሁ?

አንደበታችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ እና እርሱን ለሚያስደስተው ነገር ብቻ ተጠቀሙበት-ምስጋና እና አምልኮ፣ማንጸት እና ምክር ፡፡በእያንዳንዱ ጠዋት አንደበታችሁን በመሰዊያው ላይ አኑሩት፡፡ቃሉን በመጸለይ አንደበታችሁን ለእግዚአብሔር ስጡት፡ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያውጃል (መዝ.51፡15)፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያውጃል እናም አመሰግንሀለሁ፡፡በዙሪያዬ ላሉት ደስታን እና ህይወትን ቃላቶቼን ተጠቅሜ እንዳመጣ እና አንተን እንዳመሰግንህ እና እንዳከብርህ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon