ስህተት ስትሰራም እግዚአብሔር ይወድሃል?

ስህተት ስትሰራም እግዚአብሔር ይወድሃል?

ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለዉን የራሱን ፍቅር ያሳያል፡፡ አሁን በደሙ ከጸደቅን፣ ይልቁንማ በእርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዴት አንድንም? – ሮሜ 5:8-9

አንተ እግዚአብሔር እንዲወድህ በቂ ነኝ ብለህ አስበሀዉ ታዉቃለህ? ያለመታደል ሆኖ ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር የሚወዳቸዉ ስህተት እስካልሰሩ ድረስ ብቻ እንደሆነ ያምናሉ፡፡

ምንአልባት ይህ አስተሳሰብ ይሆናል መዝሙረኛዉን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?(መዝ 8፡4) ያለዉ፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረታት፣ የእጆቹ ሥራዎችን እንደሆንን ይነግረናል፡፡ እያንዳንዳችንን ያለ ቅድመ ሁኔታ ይወደናል፡፡

ይህንን እዉነት ተቀበል ኢየሱስ የሞተዉ ታላቅና አስደናቂ ስለሆንክ አይደለም፡፡ እርሱ የሞተዉ ስለሚወድህ ነዉ፡፡ ሮሜ 5፡8-9 እኛ ገና ኀጢአተኞች ሳለን ስለእኛ እርሱ እንደሞተልን በመንገር ይህንን ያረጋግጥልናል፡፡

እግዚአብሔር አንዲያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥህ ድረስ የወደደህ ስለ ኀጢአትህ እንዲሞት ብቻ ሳይሆን የየዕለት ስህተትህንም እንዲሸፍንልህ ነዉ፡፡እርሱ በጣም ይወዳችኋል በየቀኑ በኃይል እና በድል ውስጥ እንድትኖሩ ይፈልጋል። እግዚአብሄር ይወዳችኋል ፣ እናም እሱ እንዲያምኑ እና ሁል ጊዜ እንዲቀበሉ ይፈልጋል… ስህተት በሚሠሩበት ጊዜም እንኳን።


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ፍቅርህ ከአእምሮ በላይ ነዉ፡፡ እኔ ለራሴ ትርጉም ባጣሁ ሰዓት እንኳ ወደሀኛል፡፡ ስህተት ስሰራም አንተ ከእኔ ጋር ነህ፡፡ ዛሬ ስለማይለዋወጠዉ ፍቅርህ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon