ሶስቱ ምርጥ መሳሪያዎች

ሶስቱ ምርጥ መሳሪያዎች

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፣ እንደሰው ልማድ አንዋጋም፤፡፡ – 2 ቆሮ 10:3

ጥንቁቅ በሆነ ስልትና በማታለል ፣ ስይጣን በእናንተ ላይ ጦርነት ይከፍታል ከዚያም የተሸናፊነት አዕምሮ ይዛችሁ እንድትቀጥሉ ያደርጋችኋል፡፡ እግዚአብሔር ግን ሰይጣንን የምትረቱበትን መንፈሳዊ መሳሪያ አስታጥቋችኋል፡፡ አነዚህ ጠላታችሁን የምታሸንፉበት ሶስት ወሳኝ የሆኑ መንፈሳዊ መሳሪያዎች ናቸው፡

  1. የእግዚአብሔር ቃል፡ ከስብከት፣ ከትምህርት፣ ከንባብ እና ከግል የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት የምናገኘው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የቃሉን አብርሆት እስኪያበራላችሁ ድረስ እነዚህን ነገሮች ከቃሉ ጋር ያላችሁን ግንኙነት መቀጠል አለባችሁ፡፡
  2. ምስጋና፡ ከየትኛውም የውጊያ ስልት ይልቅ ፈጣንና ውጤታማ በሆነ መንገድ ጠላትን የምናሸንፍበት መሳሪያ ነው፡፡ ነገር ግን ምስጋናው ከልብና እውነተኛ እንጂ ከከንፈር የማይዘል ወይም ሃይማኖታዊ ስርዓት መሆን የለበትም፡፡
  3. ፀሎት፡ ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ግንኙነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ተግባቦትን ማድረግ ነው፤ እርዳታውን መጠየቅ ወይም ማንኛውም በልባችሁ ያለውን ነገር ከእርሱ ጋር የምትነጋገሩበት ነው፡፡ ፀሎት በህልውናው ውስጥ በጥሞና መሆንንና ለልባችን ሲናገረን ማዳመጥን ያካትታል፡፡ ውጤታማ የሆነ የፀሎት ህይወት እንዲኖረን፣ ከአብ ጋር የጠበቀ እና ግለሰባዊ የሆነ ግንኙነትን ማዳበር የግድ ይላል፡፡ አንድ ነገር እወቁ፣ እግዚአብሔር ይወዳችዋል፣ ሊረዳችሁም ይፈልጋል፡፡

በህይወታችሁ እየተካሄደ ያለ ጦርነት አለ፤ እግዚአብሔር ግን ከእናንተ ጎን ሆኖ ይዋጋል፤ የሚያስፈልጋችሁንም መሳሪያ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ሰይጣንን ለማፈራረስ ተጠቀሙባቸው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ጠላቴን የምንወጋበትን መንፈሳዊ መሳሪያዎች ስለሰጠኸኝ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ዛሬ፣ በአንተ እርዳታ ውጊያውን ማሸነፍ እንደምችል አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon