በመከራ ውስጥ ማመስገን

በመከራ ውስጥ ማመስገን

ሳታቋርጡ ፀልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ (በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ልትሆኑ ትችላላችሁ፣ አመስጋኝ ሁኑ)፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና፡፡ – 1 ኛ ተሰ 5፡18

መፅሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ አመስጋኝ እንድንሆን ያበረታታናል፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ፀሎትን ሲመልስና ከችግር ሲያድንን ማመስገን ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ነገሮች መጥፎ ሲሆኑብን አመስጋኝ መሆን ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ በመከራ ውስጥ እንኳን ብንሆን በአመስጋኝነታችን እንዴት ነው መቀጠል የምንችለው?

የምንመርጣቸው ሁለት ምርጫዎች አሉን፡፡ የመጀመሪያው ምንም ዓይነት ነገር በህይወታችን ቢፈጠር እግዚአብሔርን ማመስገን ነው፡፡ ወይም በሌላ አነጋገር፣ በችግራችን እና በመከራችን መሀል ሆነን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ታማኝነት እያሰብን እንዲሁም በህይወታችን የሚፈጠር ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር እንደሌለ በማወቅ መደሰት እንችላለን ማለት ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር ሆይ! ከዚህ ምንድነው ልማር የምችለው? ወደአንተ እንድቀርብና በመልካምነትህ ሙሉ በሙሉ ደስተኛ እንድሆን በዚህ በማልፍበት ሁኔታ ምን እንድማር ነው የፈለከው?›› ብለን እግዚአብሔርን መጠየቅ ሁለተኛው ምርጫችን ነው፡፡ እነዚህ ቀላል ጥያቄዎች አይደሉም፤ መልሶቹም ለመስማት ከባድ ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ ብቻ አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን ልንማር እንችላለን ፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ወደተሻሉ ነገሮች ስለሚመሯችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፡፡
በመከራ ውስጥ ስታልፉ ለእግዚአብሔር ምስጋናን ስጡ፣ ወደ ትልቅና የተሻሉ ነገሮች እንደሚመራችሁ እመኑት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ስለፍቅርህና ስለመገኘትህ አመሰግንሃለሁ፡፡ ስንት ነገሮች መልካም እንደሆኑልኝ እያስታወስከኝ ነገር ግን ነገሮች ሲበላሹብኝ ስላጉረመረምኩ ይቅር በለኝ፡፡ እኔ የምፈልገው ሁልጊዜ በአንተ መደሰት ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon