በበደሏችሁ ሰዎች ላይ መልካም ነገር ሲሆን

በበደሏችሁ ሰዎች ላይ መልካም ነገር ሲሆን

እንደዚህም በማድረጋችሁ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ፀሓዩን ለክፉዎችና ለደጎች ያወጣል፤ ዝናቡንም ለኀጢአተኞችና ለጻድቃን ያዘንባል። – ማቲ 5፡45

ሰዎች ከእግዚያብሔር ስጦታን ተቀብለው ዳሩ ግን እንደማይገባቸው ሲቆጥሩ ተመልክታችሁ ታውቃላችሁ? ሌሎች የጎዳችሁ ሰዎች መልካም ሲሆንላችሁ አይታችሁ ታውቃላችሁ?

እናንተን የጎዷችሁ ሰዎች ሲባረኩ ስታዬ ይቅርታን ማድረግ መማር አለባችሁ፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ መልካምና ክፉ ነገር በጻድቁና ፃድቅ ባልሆነው ላይ እንደሚደርስ ይናገራል። የጎዷችሁ ሰዎች በረከትን ሲቀበሉ ስታዬ ይቅርታ ማድረግ ይበልጥ ይከብዳችሁ ይሆናል ነገርግን እንድትጸልዬላቸው ተጠርታችኋልና ፀሎት አድርጉላቸው፡፡

ዛሬ እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ጎድተዋችሁ ቢሆንም እንኳን በፅሎት እንድትባርኳቸው አበረታታችኋለሁ፡፡ ስለጎዷችሁ ሰዎች ስትፀልዬ እያደረጋችሁ ያላችሁት ምርጫ ነው፡፡ ይቅርታም ደግሞ በስሜት ሳይሆን በእናንተ ውሳኔ ይሆናል፡፡ በዚህም ውስጥ ፈውስ ይሆንላችኋል፡፡

በይቅርታ የተሞላ ህይወት ክርስቶስን ለመምሰል ያግዛችኋል፡፡ የበደሏችሁን ይቀር ማለት እና በፅሎት መባረክ ጥቅሙን ስታውቁ ልባችሁ ከምሬት ይድናል ይህም መንፈሳዊ ዕድገት እግዚያብሔር ወዳዘጋጀላችሁ አላማ ይወስዳችኋል።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ፤ ምንም ያህል ከባድና አስቸጋሪ የሆነ ነገርም ቢሆን የበደሉኝን ሰዎች ይቅር ማለት እንዳለብኝና ለእነሱ መፀለይ እንዳለብኝ ተረድቼያለሁ ፤ ይቅርታ ማድረግ ምርጫ መሆኑን ተረድቻለሁ ስለዚህ ምራጫዬ ይቅር ማለት እንዲሆን እንድትረዳኝ እፀልያለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon