በእግዚአብሔር ላይ መጫን አትችሉም

በእግዚአብሔር ላይ መጫን አትችሉም

በፊቱ ቅዱሳንና ነዉር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናል፡፡ – ኤፌ 1:4

ሬ ለሁለንተናችሁ ጠቃሚ ነዉ ብዬ ያሰብሁትን አንድ ነገር ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡ እናንተ ለእግዚአብሔር ድንገተኛ አይደላችሁም፡፡ ልክ እኔን ሲመርጥ ምን ሊያገኝ እንደሚችል ያዉቅ እንደነበረ ሁሉ እናንተንም ሲመርጥ ምን ሊያገኝ እንሆነ ያዉቅ ነበር፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የራሱ ሊያደርገን እንደመረጠን ይናገራል፡፡ እናንተ በግምት አንድ ቀን በቅላችሁ እግዚአብሔርም በቃ ልቻላቸዉ ብሎ የወሰነባችሁ አይደላችሁም፡፡

እናንተ እግዚአብሔርን ልታስቸግሩት አትችሉም ምክንያቱም የመረጣችሁ እርሱ ነዉና፡፡ እግዚአብሔርን ማስገደድ አትችሉም እርሱም ችግር ሲገጥማችሁ ዓይኑን አያዞርም፡፡ በምትኩ ምን ያክር ርቀት እንደመጣችሁ፣ እንዴት እያሰራችሁ እንደሆነ፣ በፊቱ ምን ያክል ዉድ እንደሆናችሁና ምን ያክል እንደሚወዳችሁ ያስታዉሳችኋል፡፡

እግዚአብሔር ድካሞቻችሁን ቀድሞዉኑ አዉቋል፤ ያላችሁን እንከን ሁሉ፣ ስትወድቁ ሁሉ ያውቃል ነገር ግን አሁንም እንዲህ ይላል “እፈልጋችኋለሁ”፡፡ ኤፌ 1፥5 ልጆቹ ትሆኑ ዘንድ ቀድሞ እንደወሰነ ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር አባት ነዉ! በእርሱ በኩል ነገሮችህ ሁሉ እስከመጨረሻ በትክክል እንደሚሄዱ የተወሰነ ነዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ፍቅርህ አስደንቆኛል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንደ አባት መረጥከኝ፤ እኔ ምን ያህል እንከን ይኑርብኝ አንተ ግን አሁንም እንደምትፈልገኝ አዉቃለሁ፡፡ ስለ መልካምነትህ አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon