በእግዚአብሔር መኖር

በእግዚአብሔር መኖር

«… በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል» (ዮሐ.15፡7)።

ለዛሬው በተመረጠው የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ማንኛውንም «የምፈቅደውን» ነገር በክርስቶስ የምንኖር ከሆነ መጸለይ እንችላለን፣ ይሆንልንማል። ይህ የሚሆንበት ብቸኛው መንገድ የራሳችንን ፍላጎትና የእግዚአብሔርን ፍላጎት በማጣመር እኛ በእርሱ ስናድግ ይሆናል።

የእውነተኛ አማኞች ግብ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ መሆን ነው። ይህ የሚሆነው በዳግመኛ ስንወለድ በመንፈስ የሚሆን ነው። እንዲሁም ይህ የሚገለጠው በእርሱ እያደግንና እየበሰልን ስንሄድ በአዕምሮ፣ በፈቃድና በስሜት ላይ ይገለጣል። ይህን ስናደርግ ፍላጎታችን የእርሱ ፍላጎት ይሆናልና እኛ እንርሱን ስንከተል የሚመችን ነን።

የእኔና የዴቭ ለአገልግሎታችን መጠራት ለዚህ መልካም ምሳሌ ነው። የእግዚአብሔር ፍላጎት እና በአገልግሎት ውስጥ እንድንሆን ነውና ሰዎችን እንድንረዳቸው በሰጠን ጸጋ በኩል ሰዎችን እንረዳለን። ያ ደግሞ የልባችን ፍላጎት የነበረ ነበር። ለአገልግሎት የነበረው ፍላጎታችን ከእግዚአብሔር የተሰጠን ባይሆን ኖሮ ከቤተሰባችን ርቃን በመሄድ፣ በሆቴል መቆየትና ለብዙ ዓመታት በእያንዳንዱ እሁድ መጓዝ አንችልም ነበር። እርሱ ይህንን የመሰለ ጠንካራ ፍላጎት በውስጣችን በማኖር አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፍል እንድንችል ፈቃደኛ እንድንሆን ወይም ማንኛውንም ለእኛ ያለውን የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸምስንል የመጣብንን ተቃውሞ መቋቋም ቻልን።

በእግዚአብሔር መኖር ማለት ከእርሱ ጋር «አብሮ መቆየት»፣ ከእርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ በእርሱ ህልውና ውስጥ መኖር፣ በልባችን ውስጥ ያኖረውን ፍላጎት ማሳደግ፣ መንከባከብ፣ ምክንያቱም ይህ ለእና የሆነው የእርሱ ፈቃድ ነው። እርሱ ለእኛ ይናገራል እንዲሁም በእኛ በልባችን ውስጥ ሊሰጠን የሚፈልገውን በማስቀመጥ እርሱን እንድንጸልይበትና እርሱ ሊሰጠን የሚፈልገውን እንድንፈልግ በልባችን ውስጥ ያስቀምጣል። እኛ በእርሱ እስከኖርን ድረስና የምንጠይቃቸው ነገሮች የእርሱ ፍላጎት እስከሆኑ ድረስ የምንፈልገውን ፍላጎቶቻችንን ሊሰጠን እርሱ የታመነ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር «አብሮ መቆየት፡ እርሱ ትልቅ አጋር ይሆናል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon