እውነት ነጻ ያወጣችኋል

እውነት ነጻ ያወጣችኋል

እውነትን ታውቃላችሁ፤እውነትም ነጻ ያወጣችኋል፡፡ – ዮሐ 8፡32

እውነት ነው ብለን ከምናስበው እና ከምናምነው ነገር አልፈን መሄድ በፍጹም አንችልም፡፡

ዛሬ ብዙ ሰዎች በተገናዘበ ሁኔታ ስለሚያምኑበት ነገር ስለማያስቡ መላውን ህይወታቸውን እውነት ባልሆኑ አቋሞች ላይ ይመሰርታሉ፡፡መገናኛ ብዙሀን፣የዜና አውታር፣ታዋቂ ሰው ወይም ጓደኞቻቸው ያሉት ነገር ለእነርሱ እውነት ነው፡፡

ለራሳችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ከመፈለግ ይልቅ ሌሎች የሚሉትን ማመን ይወስናችሁና እግዚአብሔር እንድታደርጉ የፈጠራችሁን ነገር ከማድግ ትከለከላላችሁ፡፡እውነትን ከፈለጋችሁ ግን ያዙትና ህይወታችሁን በእርሱ ላይ ገንቡ በሁሉም አቅጣጫ የተሳካለት ሰው ትሆናላችሁ፡፡

በእግዚአብሔር እውነት ውስጥ መቆየት ከፈለጋችሁ በየዕለት ተዕለት ህይወታችሁ ከምታከናውኗቸው ነገሮች ውስጥ ከእርሱ ጋር መገናኘትን ቀዳሚ ልታደርጉት ይገባል፡፡በተደጋጋሚ በጸሎት፣ቃሉን በማንበብ፣በአምልኮ እና በቀናችሁ ላይ ስላለው ህልውናውና ምሪቱ እውቅናን በመስጠት ከእርሱ ጋር እንድትገናኙ በበቂ ሁኔታ ላበረታታችሁ ያቅተኛል፡፡

እግዚአብሔርን ስታውቁ እውነትን ታውቃላችሁ፡፡በእውነቱ መኖር ሰላምን፣ነጻነትን እና ሀሴትን ያመጣላችኋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ስለ እውነት ባለኝ አስተሳሰብ እና አቋም የተነሳ መወሰን አልፈልግም፡፡ብቸኛው የእውነት ምንጭ አንተ ነህ፡፡ከአንተ ጋር በመገናኘት ጊዜ ሳሳልፍ እውነትህን አሳየኝ፣ወደ እውነትህም ምራኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon