እግዚአብሔርን “ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ” ከመፈለግ መውጣት

እግዚአብሔርን “ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ” ከመፈለግ መውጣት

እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፣የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን? – 1 ኛ ቆሮ 3፡16

እግዚአብሔር ጋር ጊዜ የማሳልፈው አንዳንዴ ወይም ህይወቴ ከባድ ችግር ውስጥ ሲገባ ብቻ ነበር፡፡ከጊዜ በኋላ ግን ከአንድ ድንገተኛ ነገር ወደሌላው እየተሸጋገርኩ መኖር ማቆም ከፈለግሁ በእያንዳንዱ ቀን እግዚአብሔርን እጅግ እንደሚያስፈልገኝ ነገር መፈለግ እንዳለብኝ ተማርሁ፡፡

ሁልጊዜም ወደ እርሱ ስንመጣ እግዚአብሔር እንደሚረዳን እውነት ነው፡፡ቋሚ ድል ከፈለግን ግን እግዚአብሔርን “ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ” ከመፈለግ ህይወት አውጥተን ወደ ዕለት ተዕለት ኑሯችን መጋበዝ አለብን፡፡

እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ግላዊ ግንኙነት ውስጥ እንድንገባ ይፈልጋል፡፡ይሄንን ደግሞ በእኛ ውስጥ በመኖር አረጋግጦልናል፡፡

ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞት ሁሉን ከሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር ግላዊ በሆነ የምናሳልፍበትን መንገድ ከፍቶልናል፡፡እግዚብሔር ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ እንድንፈልገው ቢፈልግ ኖሮ አንዳንዴ ይጎበኘናል እንጂ በቋሚነት ለመኖር ወደ እኛ አይመጣም፡፡

ምን አይነት የሚገርም ሀሳብ ነው! እግዚአብሔር የግል ጓደኛህ ነው!ዛሬ “ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ” እግዚአብሔርን መፈለግን ታቆማላችሁ?


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ የክርስትና ህይወት ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ ከመጠቀሚያነት እጅግ የሚበልጥ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ችግር ባጋጠመኝ ቁጥር አንተን ከመጥራት ይልቅ በእኔ ውስጥ ስለምትኖር እንደ የግል ጓደኛ ላውቅህ እፈልጋለሁ፡፡በእያንዳንዱ ቀን ልፈልግህ እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon