እግዚአብሔር ለአንተ ያለዉ ዓላማ ታላቅ ነዉ

እግዚአብሔር ለአንተ ያለዉ ዓላማ ታላቅ ነዉ

እያንዳንዱ የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም በኋላ፣ ከሌላ ሰዉ ጋር ራሱን ሳያወዳድር፣ ስለራሱ የሚመካበትን ያገኛል፡፡ – ገላ 6:4

ኛ ራሳችንን ከማንም ጋር ከማነጻጸር መቆጠብ ያስፈልገናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንድንበሳጭና እርሱ ለእኛ ሊሰጥ ያሰበዉን በረከት ለመቀበል ብቁዎች እንዳልሆንን እንድናስብ አይፈልግም፡፡

የእኛን ኑሮ ከሌሎች ሰዎች ኑሮ ጋር ማነጻጻር ለእኛም ለእነርሱም ጥሩ አይደለም፡፡ ለሌሎች ጥሩ የማይሆነዉ እነርሱ በሚያዉቁትና ባለቸዉ ነገር መቅናት ስለምንጀምር ቅር እናሰኛቸዋለን፡፡ ከዚያም እነርሱን እግዚአብሔር እንደሰራቸዉ ግሩም ሰዎች ማድነቅ አንችልም፡፡

ለእኛ ልክ የማይሆነዉ እግዚአብሔር ለህይወታችን ያለዉን ዓለማ ስለሚገድብ ነዉ፡፡ ንጽጽር እግዚአብሔርን የሚለዉ እንዲህ ነዉ “አንተ በህይወቴ ያለህን ሥራ ዉስን ማድረግ እፈልጋለሁ፣ እኔ መሆን የምፈልገዉ ልክ እንደሌላ ሰዉ ነዉ”

ነገር ግን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ግለሰባዊ ዕቅድ አለዉ፡፡ ለአንተ ያለዉ እቅድ ልትገምተዉ ከምትችለዉ በላይ ነዉ፡፡ እርሱ ለአንተ ባለዉ እቅድ በመሄድ እነዚያ እቅዶች የሚያመጡትን በረከት ለመቀበል የሌሎች ዕቅድ ማየት አቁም፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ራሴን በሐቀኝነት እንድፈትንና ራሴን ከሌሎች ጋር በማነጻጸሬ ምክንያት በዉስጤ ያደጉትን ቅናት፣ ቅሬታና ፍርሃት እንዳጋልጥ እርዳኝ፡፡ አንተ እንድሆነዉ የፈለግከዉን መሆንና ለእኔ ያሰብከዉን ህይወት መኖር እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon