እግዚአብሔር ከእፍረታችሁ ነጻ ሊያወጣችሁ ይችላል

እግዚአብሔር ከእፍረታችሁ ነጻ ሊያወጣችሁ ይችላል

ህዝቤ በእፍረታቸው ፈንታ እጥፍ ይቀበላሉ፣በውርደታቸው ፈንታ በርስታቸው ደስ ይላቸዋል፤የምድራቸውንም ዕጥፍ ርስት ይወርሳሉ፤ዘላለማዊ ደስታም የእነርሱ ይሆናል፡፡ – ኢሳ 61፡7

ሀጢያትን ከመስራታቸው በፊት ህይወት ለአዳም እና ለሔዋን ምን ይመስል ነበር ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?

ዘፍጥረት2፡25 ምንም እንኳ አዳም እና ሔዋን በኤደን ገነት ውስጥ ራቁታቸውን የነበሩ ቢሆንም አይተፋፈሩም ነበር ሲል ይነግረናል፡፡ልብስ እንዳልለበሱ ከመናገር በተጨማሪ ይሄ ክፍል በምንም አይነት ጭምብል ጀርባ ሳይደበቁ፣ ምንም አይነት ጨዋታ ሳይጫወቱ አንዳቸው ለሌላው ሙሉ በሙሉ ታማኝ እና ግልጽ እንደነበሩ-ያመለክታል ብዬ አምናለሁ፡፡የእፍረት ስሜት ስላልነበረባቸው እራሳቸውን ለመሆን ነጻ ነበሩ፡፡ሀጢያትን ከሰሩ በኋላ ግን እራሳቸውን ደበቁ(ዘፍ.3፡6-8ን ይመልከቱ)፡፡

በክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ከከባድ የሀጢያት እፍረት ጋር እንኖር ነበር፡፡ነገር ግን በእርሱ መስዋዕትነት የተነሳ የሰው ልጆች ፍጹም የሆነ ነጻነትን እርስ በእራሳቸው እና ከእግዚአብሔር ጋር ለመደሰት መልካም አጋጣሚን አገኙ፡፡

ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ቃል ነጻ መውጣት እንደምንችል ተስፋ ቢሰጠንም እና ቢያረጋግጥልንም እንደአለመታደል ሆኖ ብዙዎቻችን በሀፍረት ቀንበር ስር እስካሁን እንኖራለን (ኢሳ.61፡7ን ይመልከቱ)፡፡

እግዚአብሔር ከሀፍረት ነጻ ሊያወጣችሁ ይችላል፡፡በውስጣችሁ ለማደግ ከተነሳው ሀፍረት ነጻ እንዲያወጣችሁ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠይቁት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ለእኔ በመስቀል ላይ የገዛህልኝን ከሀፍረት ነጻ መሆን እቀበላለሁ፡፡ከዚህ በኋላ አልደበቅም፣የማልጠቅም ሰው እንደሆንኩም አላስብም፡፡ሀጢያቴን ስለደመሰስከው በአንተ ፊት ነጻ እና ግልጽ ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon