እግዚያብሔር የትኛውንም ጉድፍ ያነፃል

እግዚያብሔር የትኛውንም ጉድፍ ያነፃል

ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት። – ዕብ 11፡6

በህጻንነቴ እጅግ በጣም በከፋ መልኩ ጥቃት ተፈፅሞብኛል፡፡ ህይወቴ አሰቃቂ ነበር፡፡ በዕድሜየ 20ዎቹ ከመድረሴ በፊት ደስተኛ ሆኜ አላውቅም ነበር። አዕምሮየየ ቆሽሾ ነበር፤ ስሜቴ የቆሸሸና የተተራመሰ ነበር ሁሉም ነገር ተተራምሶና ጎድፎ ነበር፡፡

ነገርግን ክብር ለእግዚያብሔር ይሁን እንደዚያ ሆኜ አልቀረሁም እግዚያብሔር ካለሁበት ሁኔታ አውጥቶኝ ነገሮቼን ቀይሯቸዋል፡፡ አሁን ከእግዚያብሔር ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለኝ፤ ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ ጋር መልካም ግንኙነት መስርቼያለሁ፡፡ አሁን እግዚያብሄር እንዳደርገው የጠራኝን ነገር እያደረኩ ነው፡፡

ዕብ 11፡6 ላይ የእግዚያብሔር ቃል የሚነግረን እግዚያብሔር በትጋትና በታታሪነት ያገለገሉትን ዋጋ እንደሚሰጥ ነው፡፡ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ማንኛውም ወደ እርሱ ለመቅረብ የከፈልኩት መስዋዕትነት ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ታላቅ ዋጋ አላቸው ሁሌም እየሰጠኝ ያለው ደግሞ የሚበልጠውን ነው፡፡ ምናልባት ጆይስ አሁን እኔ በምን ውስጥ እያለፈኩ እንደሆነ አታውቂም በጣም ከባድ ነው እያላችሁ ይሆናል፡፡

እረዳለሁ በእዲህ አይነት ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ እኔም ነበርኩበት፡፡ ነገርግን እግዚያብሔር እርሱን የሚፈልጉትን ዋጋቸውን ይሰጣል፡፡በከባድ ጊዜያችሁም ቢሆን እግዚያብሔርን በትጋት ፈልጉ እሱ የእናንተን ትርምስ ማስተካከል ይችላል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ መልክ ያጡ ነገሮቼን ልታስተካከል እንደምትችል አምናለሁ በችግሮቼ መካከል ከመቆም ይልቅ ከልቤ ዛሬ እፈልግሃለሁ በህይወቴም መልካም እንደምታደርግ እጠብቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon