ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርግ

ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት አድርግ

« … እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው» (1ኛ ዮሐ.1፡3)።

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ህብረት ሊያደርግ ይፈልጋል። በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ዮሐንስ ከአባትና ከልጁ ጋር ህብረት እንዳለን ሲጽፍ እንደሁም ጳውሎስ ደግሞ በ2ኛ ቆሮ. 13፡14 ላይ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለን ህብረት ይጽፋል። የመንፈስ ቅዱስ ህብረት ከመንፈስ ቅዱስ ከራሱና ከሌሎች አማኞች ጋር ስላለን ህብረት የሚናገር ነው። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ የሚኖር ስለሆነ ነው። ከእርሱ ጋር ህብረት ለማድረግና አንድነትን ለመፍጠር ወደ ሩቅ መሄድ አይገባህም።

ምናልባትም የህብረትን ምንነት በትክክል ለማስረዳት ጥሩ አጋር /አብሮነት/ የሚገለጠው የሁለት ሰዎች አብሮ መኖርን በምሳሌነት ልጠቀም። ለምሳሌ ባልና ሚስት፤ እኔ በቤቴ ከባለቤቴ ዴቭ ጋር እኖራለሁ። እና እጅግ በጣም እንቀራረባለን። አብረን እንሠራለን፣ ብዙ ወሳኝ ነገሮችን አብረን ሠርተናል። እርሱ የገልፍ ስፖርት ለመጫወት የሚሄድበት ጊዜ ነበር እና በስልክ ንግግር እናደርጋለን። እርሱ ምናልባት በቴሌቪዥን ስፖርት ሲመለከት እኔ በተለየ ሁኔታ ለእነዚህ ነገሮች ፍላጎት ባይኖረኝም አሁንም በቤት ውስጥ አለሁ። እኔና ዴቭ አብረን እንመገባለን፣ እንተኛለን፣ በማለዳ ተነስተን በቀኑ ወደ ምንሄድበት ከመሄዳችን በፊት አብረን ሰውነታችንን እንታጠባለን። ለብዙ ጊዜያት በእርስበርሳችን አብሮነት እናሳልፋለን። ሁልጊዜ አናወራም ነገር ግን ሁልጊዜ እርስበርሳችን እንተዋወቃለን። የጥሞና ጊዜ ሲኖረን አብረን በትልቅ መነፋፈቅ እንገኛኛለን።

እኔ ለዴቭ ለእኛ ጠቃሚ ስለሆኑና ጠቃሚ ስላልሆኑ ነገሮች አወራለታለሁ። እርሱም በተመሳሳይ ነገር ያደርጋል። አንዳችን በምንናገርበት ጊዜ ሌላችን እንሰማለን። በዚህ ቀለል ባለ ሁኔታ ህብረት ማለት አብሮ ስለመሆን ነው። አንዱ ሲያወራ ሌላው ማዳመጥ። መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር አለ። እርሱ በእኛ ይኖራልና፣ ፈጽሞ አይለየንም። ለእርሱ መናገር እንችላለን። እርሱ ይሰማናል። እንዲሁ እርሱ በሚናገርበት ጊዜ እና ደግሞ ልንሰማው ያስፈልገናል።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ከእግዚአብሔር ጋር በተመቻቸ ሁኔታ ለመሆን ማወቅ አለብህ። በቤትህ እንደተከበረ እንግዳ አስተናግደው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon